Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 21:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ትዕቢተኛና ትምክሕተኛ ሰው ፌዘኛ ነው፤ ድርጊቱም በትዕቢት የተሞላ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ትዕቢተኛና ኵሩ ሰው “ፌዘኛ” ይባላል፤ በጠባዩም እብሪተኛ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ኩሩና ተጓዳጅ ሰው ፌዘኛ ይባላል፥ እርሱም በትዕቢት ቁጣ ያደርጋል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የችኩል፥ የነዝናዛና የነገረኛ ሰው ስሙ ቸነፈር ነው፥ ክፉን የሚያስብም ኃጥእ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 21:24
15 Referências Cruzadas  

በክፉ ሰዎች ምክር የማይሄድ፥ የኃጢአተኞችን መንገድ የማይከተል፥ ከፌዘኞች ጋር ኅብረት የማያደርግ የተባረከ ነው።


“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!


ትዕቢት ወደ ጥፋት ይወስዳል፤ ትምክሕተኛነትም ወደ ውድቀት ያደርሳል።


ትዕቢት ጥፋትን ያመጣል፤ ትሕትና ግን ክብርን ያጐናጽፋል። ክብርን ግን ትሕትና ይቀድመዋል።


ለፌዘኞች ፍርድ፥ ለሞኞችም ግርፋት ተዘጋጅቶላቸዋል።


ሞኝ ሁልጊዜ የሚያስበው ኃጢአትን ስለ ማድረግ ነው፤ ፌዘኛን ሰዎች ሁሉ ይጠሉታል።


እግዚአብሔር ፌዘኞችን ይንቃል፤ ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል።


በንቀት የሚመለከት ዐይን፥ ሐሰትን የሚናገር ምላስ፥ ንጹሖች ሰዎችን የሚገድሉ እጆች፥


የይሁዳ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “የሞአብ ሕዝብ ምን ያኽል ኩራተኛ መሆኑን፥ ትዕቢተኛነቱን፥ ዕብሪተኛነቱንና ንቀቱን ሰምተናል፤ ነገር ግን ፉከራው ሁሉ ከንቱ ነው።”


ጨካኞችና ፌዘኞች ይጠፋሉ፤ ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይደመሰሳሉ።


ሞአብ በከፍተኛ ኲራት፥ ራሷን ከፍ ከፍ በማድረግ በትዕቢተኛነት፥ በመጀነንና በልበ ደንዳናነት የተወጠረች መሆንዋን ሰምቼአለሁ።


በእርግጥ ሀብት ሰውን ያታልላል፤ ትምክሕተኛ ሰው ዕረፍት የለውም፤ እንደ መቃብር ስስታም እንደ ሞትም በቃኝ የማይል ስለ ሆነ መንግሥታትን ሁሉ ለራሱ ይወራል፤ ሕዝቦችንም ይማርካል።


ከዚያ በኋላ ሄሮድስ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎቹ እንዳታለሉት በተገነዘበ ጊዜ፥ በጣም ተቈጣ፤ ወደ ቤተልሔምና በዙሪያዋም ወዳሉት መንደሮች ሁሉ ወታደሮቹን ልኮ፥ ከከዋክብት ተመራማሪዎቹ በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ዕድሜአቸው ሁለት ዓመት የሆናቸውንና ከዚያ በታች የሆኑትን በቤተልሔምና በአካባቢው የነበሩትን ወንዶች ሕፃናትን አስገደለ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios