Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 21:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የተቈጣ ሰው ስጦታ በድብቅ ሲቀርብለት ንዴቱ ይበርድለታል፤ በምሥጢር የሚሰጥ እጅ መንሻ ቊጣን ያበርዳል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በስውር የተደረገ ስጦታ ቍጣን ያበርዳል፤ በጕያ የተሸሸገ እጅ መንሻም ታላቅ ቍጣን ጸጥ ያደርጋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስጦታ በስውር ቁጣን ታጠፋለች፥ የብብትም ውስጥ ጉቦ ጽኑ ቁጣን ታበርዳለች።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በስውር ያለ ስጦታ ቍጣን ይመልሳል፥ ስጦታን የሚሸልግ ግን ጽኑ ቍጣን ያስነሣል።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 21:14
8 Referências Cruzadas  

‘በተለይም አገልጋይህ ያዕቆብ ከበስተኋላ እየመጣ ነው’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው። ይህንንም ያለበት ምክንያት “እኔ ከመድረሴ በፊት በሚደርስለት ስጦታ ቊጣውን አበርድ ይሆናል፤ በኋላም በማገኘው ጊዜ በደስታ ይቀበለኛል” በሚል ሐሳብ ነው።


አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ መሄዳችሁ የማይቀር ከሆነ ለአገረ ገዢው ገጸ በረከት የሚሆን ምድራችን ከምታፈራው ምርጥ ነገር ሁሉ በስልቻዎቻችሁ ጨምራችሁ ሂዱ፤ ይኸውም በለሳን፥ ማር፥ ቅመማ ቅመም፥ ከርቤ፥ ተምርና ለውዝ ይዛችሁ ሂዱ።


ክፉ ሰው ፍርድን ለማጣመም፥ በምሥጢር ጉቦ ይቀበላል።


አንዳንድ ሰዎች ጉቦ እንደ አስማት የሚሠራ ይመስላቸዋል፤ ጉቦ በመስጠትም ሁሉ ነገር ይሳካልናል ብለው ያምናሉ።


ስጦታ ለሰጪው መንገድን ይከፍትለታል፤ ወደ ትልልቆች ሰዎችም ፊት መቅረብ ያስችለዋል።


ብዙ ሰዎች የለጋሥ ሰውን ወዳጅነት ይፈልጋሉ፤ ስጦታን ለሚሰጥ ሰው ሁሉም ወዳጁ ነው።


ከዚያም በኋላ ዳዊት ያመጣችለትን ስጦታ ተቀብሎ “ወደ ቤትሽ በሰላም ተመልሰሽ ሂጂ፤ ልመናሽን ሰምቼአለሁ፤ የጠየቅሽውን ሁሉ አደርጋለሁ” አላት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios