Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 19:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከሰው የሚፈለገው ታማኝነት ነው፤ ሐሰተኛ ከመሆን ይልቅ ድኻ መሆን ይሻላል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሰው የሚመኘው ጽኑ ፍቅር ነው፤ ውሸታም ከመሆንም ድኻ መሆን ይሻላል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የሰው ቸርነት የእርሱ ፍሬ ነው፥ ከሐሰተኛ ሀብታምም እውነተኛ ድሀ ይሻላል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ምጽዋት ለሰው ፍሬ ነው፤ ከሐሰተኛ ባለጠጋም እውነተኛ ድሃ ይሻላል።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 19:22
14 Referências Cruzadas  

አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤


እግዚአብሔር ግን ‘ለእኔ ቤተ መቅደስን ለመሥራት በመፈለግህ መልካም አድርገሃል፤


ገንዘብ ለማግኘት ብሎ ባልንጀራውን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥ ግፉ በልጆቹ ላይ ይደርሳል።


ወንድሞቼ ግን ጐርፉ ከወረደ በኋላ እንደሚደርቁና እንደማያስተማምኑ ወንዞች አታላዮች ናቸው።


ተራ ሰዎች እንደ አየር ናቸው፤ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ተጨባጭነት እንደሌለው ምኞት ናቸው፤ ሁለቱ በሚዛን ላይ ቢቀመጡ ከነፋስ ሽውታ ይቀላሉ።


በንግግሩ ከሚቀላምድ ሞኝ ሰው ይልቅ በቅንነት የሚኖር ድኻ ሰው ይሻላል።


ሰዎች ብዙ ነገር ያቅዳሉ፤ ተፈጻሚነትን የሚያገኘው ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።


እግዚአብሔርን ብትፈራ ረጅም ዕድሜ ይኖርሃል፤ ጒዳት ሳይደርስብህ በደስታና በሰላም ትኖራለህ።


ለመስጠት መልካም ፈቃድ ካለ የሰው ልግሥና ተቀባይነት የሚያገኘው ባለው መጠን ሲሰጥ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለም።


ይህም እምነት በዘለዓለም ሕይወት ተስፋ ላይ የተመሠረተ ነው፤ የማይዋሸው አምላክ ይህን ሕይወት ለመስጠት ከዘመናት በፊት ቃል ገባልን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios