Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 17:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ደስተኛነት ለልብ መልካም መድኃኒት ነው፤ የመንፈስ ሐዘንተኛ መሆን ግን አጥንትን ይሰብራል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኀኒት ነው፤ የተሰበረ መንፈስ ግን ዐጥንትን ያደርቃል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፥ ያዘነች ነፍስ ግን አጥንትን ታደርቃለች።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ደስ ያላት ልብ ፈውስን ታገኛለች፤ ኀዘንተኛ ሰው ግን አጥንቱን ያደርቃል።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 17:22
12 Referências Cruzadas  

ጒሮሮዬ እንደ ሸክላ ደረቀ፤ ምላሴም ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤ እንደ ሞተ ሰው በትቢያ ላይ ተውከኝ።


በሐሳብ መጨነቅ ሐዘንን ያመጣል፤ በጎ ንግግር ግን ያስደስታል።


የልብ ደስታ ፊትን ያበራል፤ የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ያደቃል።


መልካም ንግግር እንደ ማር. ወለላ ይጣፍጣል፤ ለሰውነትም ፈውስ የሚሰጥ ነው።


ጠንካራ መንፈስ ሕመምን ያስታግሣል፤ መንፈሱ የደከመውን ግን ማንም አይረዳውም።


ሳቅ ከሞኝነት ያልተሻለ፥ ተድላ ደስታም ዋጋ የሌለው ነገር መሆኑን አስተዋልኩ።


ስለዚህ ይህ ሰው በጣም ከማዘኑ የተነሣ ተስፋ እንዳይቈርጥ ይልቅስ ይቅርታ እንድታደርጉለትና እንድታጽናኑት ይገባል።


እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን ሐዘን ወደ መዳን የሚመራ በንስሓ የሚገኘውን ለውጥ ስለሚያስገኝ ጸጸትን አያስከትልም፤ ዓለማዊ ሐዘን ግን ሞትን ያመጣል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios