Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 4:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የእነርሱም አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኙትን ንዋያተ ቅድሳት መንከባከብ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የቀዓታውያን ሥራ ንዋየ ቅድሳቱን መጠበቅ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በመገናኛው ድንኳን በንዋየ ቅድሳቱ ዘንድ የቀዓት ልጆች ሥራ ይህ ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሥራ ይህ ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በመገናኛው ድንኳን በንዋየ ቅድሳቱ ዘንድ የቀዓት ልጆች ሥራ ይህ ነው፤

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 4:4
11 Referências Cruzadas  

ዳዊት ሌዋውያንን በየጐሣቸው ክፍል መሠረት በሦስት ቦታ መደባቸው፤ እነርሱም ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።


ከዚህ በኋላ የሌዋዊው የቀዓት ጐሣ የሆኑት ሰዎች ንዋያተ ቅድሳትን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱ ወደሚቀጥለው ሰፈር ከመድረሳቸው በፊት ድንኳኑ እንደገና መተከል ነበረበት።


ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው።


ወደ ተቀደሰው ስፍራ ተጠግተው እንዳይሞቱ እንዲህ አድርግላቸው፦ አሮንና ልጆቹ ወደ መቅደሱ ገብተው የያንዳንዱን ሰው ሥራና ሸክሙን ይመድቡለት።


እነርሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን የመሸከም ኀላፊነት ይኖራቸዋል።


በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል ብቃት ያላቸውን፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ እስከ ኀምሳ የሚደርሰውን ወንዶች ሁሉ መዝግብ።


በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ እስከ ኀምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቊጠር፤


“ሕዝቡ ከሰፈረበት ቦታ በሚነሣበት ጊዜ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳኑ ገብተው፥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን መጋረጃ በማውረድ የኪዳኑን ታቦት በእርሱ ይጠቅልሉት።


በእነርሱ ኀላፊነት የሚጠበቁት ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው የሚሸከሙአቸው ስለ ሆኑ ሙሴ ለቀዓታውያን ሠረገሎችንም ሆነ በሬዎችን አልሰጣቸውም።


ይህም፥ ቤቱን ትቶ ወደ ሩቅ አገር የሄደውን ሰው ይመስላል፤ እርሱም እያንዳንዱን አገልጋይ በልዩ ልዩ የሥራ ኀላፊነት ላይ መደበ፤ ዘበኛውንም ተግቶ እንዲጠብቅ አዘዘው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios