Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 22:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 መልአኩ ግን “ከእነዚህ ሰዎች ጋር መሄዱን ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ ተናገር” አለው፤ በዚህ ዐይነት በለዓም ከባላቅ ባለሥልጣኖች ጋር ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 የእግዚአብሔርም መልአክ በለዓምን፣ “መሄዱን ከሰዎቹ ጋራ ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ ተናገር” አለው። ስለዚህ በለዓም ከባላቅ አለቆች ጋራ ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 የጌታም መልአክ በለዓምን፦ “ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ” አለው። በለዓምም ከባላቅ ሹማምንት ጋር ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በለ​ዓ​ምን፥ “ከሰ​ዎቹ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ና​ገ​ር​ህን ቃል ብቻ ለመ​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። በለ​ዓ​ምም ከባ​ላቅ አለ​ቆች ጋር ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 የእግዚአብሔርም መልአክ በለዓምን፦ ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምናገርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ አለው። በለዓምም ከባላቅ አለቆች ጋር ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 22:35
8 Referências Cruzadas  

ሚክያስ ግን “እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ቃል ብቻ የምናገር መሆኔን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ!” ሲል መለሰለት።


ስለዚህ በልበ ደንዳናነታቸው አካሄድ እንዲሄዱ፥ የፈለጉትንም ነገር እንዲያደርጉ ተውኳቸው።


ታማኝ ሰው በሰላም ይኖራል፤ ጠማማ ሰው ግን በጒድጓድ ውስጥ ይወድቃል።


ባላቅ የበለዓምን መምጣት በሰማ ጊዜ እርሱን ለመቀበል በሞአብ ጠረፍ በአርኖን ወንዝ ዳር ወደምትገኘው ወደ ዔር ከተማ ሄደ።


እኔ ግን በለዓምን አልሰማሁትም፤ ስለዚህም በመርገም ፈንታ ባረካችሁ፤ በዚህም ዐይነት ከባላቅ እጅ አዳንኳችሁ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios