Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 11:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በግብጽ ሳለን ምንም ዋጋ ሳንከፍል የፈለግነውን ያኽል ዓሣ እንበላ እንደ ነበረ እናስታውሳለን፤ በዚያ ሳለን እንበላ የነበረውን ዱባ፥ (ኪያር) ሀብሀብ (በጢኽ)፥ ኲራት (ድንች መሳይ ምግብ) ቀዩንና ነጩን ሽንኩርት፥

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በግብጽ ያለ ምንም ዋጋ የበላነው ዓሣ እንዲሁም ዱባው፣ በጢኹ፣ ኵራቱ፣ ነጭ ሽንኵርቱ ትዝ ይለናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በግብጽ ሳለን እንዲያው በነጻ እንበላው የነበረውን ዓሣ፥ ዱባውንም፥ ሐብሐብውንም፥ ባሕሮውንም፥ ቀዩንም ሽንኩርት፥ ነጩንም ሽንኩርት እናስታውሳለን፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በግ​ብፅ ያለ ዋጋ እን​በ​ላው የነ​በ​ረ​ውን ዓሣ፥ ዳቦ​ው​ንም፥ በጢ​ኹ​ንም፥ ኩራ​ቱ​ንም፥ ቀዩ​ንም ሽን​ኩ​ርት፥ ነጩ​ንም ሽን​ኩ​ርት ቍንዶ በር​በ​ሬ​ው​ንም እና​ስ​ባ​ለን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በግብፅ ያለ ዋጋ እንበላው የነበረውን ዓሣ፥ ዱባውንም፥ በጢኹንም፥ ኩራቱንም፥ ቀዩንም ሽንኩርት፥ ነጩንም ሽንኩርት እናስባለን፤

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 11:5
7 Referências Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! የሕይወታቸው ድርሻ የዚህ ዓለም ነገር ብቻ ከሆነ ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ለምትወዳቸው ምግብን ስጣቸው፤ ልጆቻቸው ብዙ ይኑራቸው፤ የልጅ ልጆቻቸውም የተትረፈረፈ ምግብ እንዲኖራቸው አድርግ።


“ምነው በግብጽ ሳለን እግዚአብሔር በገደለን ኖሮ፥ በዚያ ሌላው ቢቀር ሥጋም ሆነ ሌላ ምግብ የፈለግነውን ያኽል መመገብ እንችል ነበረ፤ እናንተ ግን ሁላችንም በራብ እንድናልቅ ወደዚህ በረሓ አወጣችሁን።”


የጽዮን ልጅ በወይን አትክልት ቦታ ውስጥ እንዳለ ዳስ በዱባ ተክል ውስጥ እንዳለ ጎጆና እንደ ተከበበች ከተማ ሆናለች


ደግሞም ‘እኛ የጦርነት ወሬና የእምቢልታ ድምፅ ወደማይሰማባት፥ ራብም ወደሌለባት ወደ ግብጽ ወርደን በዚያ እንኖራለን’ ብትሉ፥


ነገር ግን ለሰማይ ንግሥት የሚቃጠል መሥዋዕትና ለእርስዋም የወይን ጠጅ መባ ማቅረብን ካቋረጥንበት ጊዜ ጀምሮ ምንም ያተረፍነው ነገር የለም፤ ሕዝባችንም በጦርነትና በረሀብ አልቆአል።”


በሙሴና በአሮንም ላይ እንዲህ እያሉ አጒረመረሙ፥ “በግብጽ ሳለን ወይም በዚህ ምድረ በዳ ሞተን በቀረን መልካም በሆነ ነበር!


የእነርሱ አምላክ ሆዳቸው ነው፤ አሳፋሪ የሆነ ነገር ለእነርሱ ክብራቸው ነው፤ ሐሳባቸውም የሚያተኲረው በምድራዊ ነገር ላይ ነው፤ ስለዚህ የእነርሱ መጨረሻ ጥፋት ነው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios