Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ነህምያ 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሐኑንና የዛኖሐ ነዋሪዎች ተባብረው የሸለቆውን ቅጽር በር በማደስ ሠሩ፤ ለቅጽር በሩም መዝጊያዎችን አቁመው ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጁለት፤ እስከ ጒድፍ መጣያ ቅጽር በር 440 ሜትር ርዝመት ያለውንም ቅጽር እንደገና ሠሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “የሸለቆ በር” ተብሎ የሚጠራውን የሐኖንና የዛኖ ነዋሪዎች ዐደሱት፤ መልሰው ሠሩት፤ ከሠሩትም በኋላ መዝጊያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ፤ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹንም አበጁ። እንዲሁም የቈሻሻ መጣያ በር ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን አንድ ሺሕ ክንድ ቅጥር መልሰው ሠሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሐኑንና የዛኖሐ ሰዎችም “የሸለቆ በር” አደሱ፤ መልሰው ሠሩት፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጁ፤ ደግሞም እስከ “የፍግ በር” ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር ሠሩ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሐኖ​ንና የዘ​ናን ሰዎ​ችም የሸ​ለ​ቆ​ውን በር አደሱ፤ ሠሩት፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፥ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ፤ ደግ​ሞም እስከ ጕድፍ መጣያ በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚ​ሆን ቅጥር ሠሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሐኖንና የዛኖዋ ሰዎችም የሸለቆውን በር አደሱ፥ ሠሩት፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ፥ ደግሞም እስከ ጉድፍ መጣያው በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር ሠሩ።

Ver Capítulo Cópia de




ነህምያ 3:13
7 Referências Cruzadas  

ዖዝያ በማእዘን ቅጽር በር፥ በሸለቆ ቅጽር በርና በቅጽሩም መጠምዘዣ ላይ መቈጣጠሪያ ግንቦችን በመሥራት የኢየሩሳሌምን ምሽጎች አጠናከረ፤


በዛኖሐ፥ በዐዱላምና በእነዚህም ከተሞች አጠገብ በሚገኙት መንደሮች ሁሉ ይኖሩ ነበር፤ ላኪሽና በአቅራቢያዋ የሚገኙ የእርሻ ቦታዎች፥ ዐዜቃና የአካባቢዋ መንደሮች ሁሉ የእነርሱ መኖሪያዎች ነበሩ፤ በዚህ ዐይነት የይሁዳ ሕዝብ መኖሪያ በደቡብ ከቤርሳቤህ፥ በሰሜን ከሂኖም ሸለቆ በመለስ ባለው ክልል ውስጥ ነበር።


በሸለቆ ቅጽር በር ወጥቼ የዘንዶ ምንጭ ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ በማለፍ፥ በስተ ደቡብ ወደሚገኘው የጒድፍ መጣያ ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ ሄድኩ፤ ጊዜውም ገና ሌሊት ነበር፤ በማልፍበትም ጊዜ የፈራረሱትን የከተማይቱን ቅጽሮችና በእሳት የወደሙትን የቅጽር በሮች ጐበኘሁ።


ስለዚህ ሌሊቱን ወደ ቄድሮን ወንዝ በመውረድ፥ ቅጽሮችን እየጐበኘሁ አልፌ ሄድኩ፤ በመጨረሻም በዚያው በመጣሁበት መንገድ ተመልሼ በሸለቆው ቅጽር በር በኩል ወደ ከተማይቱ ገባሁ።


ዛኖሐ፥ ዔንጋኒም፥ ታፑሐ፥ ዔናም፥


ኢይዝራኤል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖሐ፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios