Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 15:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ይህ ልጅህ ግን ሀብትህን ከአመንዝራ ሴቶች ጋር አባክኖ በተመለሰ ጊዜ የሰባውን ወይፈን ዐረድክለት።’

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ነገር ግን ይህ ልጅህ ንብረትህን ከጋለሞቶች ጋራ አውድሞ ሲመጣ፣ የሠባውን ፍሪዳ ዐረድህለት።’

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ነገር ግን ይህ ልጅህ ገንዘብህን ከአመንዝራ ሴቶች ጋር አባክኖ በመጣ ጊዜ፥ የሰባውን ፍሪዳ አረድህለት፤’ አለው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ገን​ዘ​ብ​ህን ሁሉ የጨ​ረሰ ይህ ልጅህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ግን የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረ​ድ​ህ​ለት።’

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ነገር ግን ገንዘብህን ከጋለሞቶች ጋር በልቶ ይህ ልጅህ በመጣ ጊዜ፥ የሰባውን ፊሪዳ አረድህለት አለው።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 15:30
10 Referências Cruzadas  

ሙሴ ግን እግዚአብሔር አምላኩን በመማለድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ በሥልጣንህና በታላቅ ኀይልህ ከግብጽ ምድር ያወጣኸውን ሕዝብህን እስከዚህ የምትቈጣው ስለምነው?


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብጽ ምድር መርተህ ያወጣኸው ሕዝብህ ራሱን ስላረከሰ ፈጥነህ ውረድ፤


ጥበብን የሚወድ አባቱ ያስደስታል፤ አመንዝሮችን የሚከተል ግን ሀብቱን ያባክናል።


ሌሎቹ ሁሉ የሰጡት ካላቸው ሀብት የተረፋቸውን ነው፤ እርስዋ ግን ድኻ ሆና ሳለች ምንም ሳታስቀር ያላትን ሁሉ ሰጠች።”


ልጁ ግን ለአባቱ እንዲህ ሲል መለሰ፤ ‘እነሆ! ይህን ያኽል ዓመት አገለገልኩህ፤ ከትእዛዝህም ከቶ ዝንፍ ብዬ አላውቅም፤ ታዲያ እኔ ከጓደኞቼ ጋር የምደሰትበት አንድ ጠቦት እንኳ ሰጥተኸኝ አታውቅም!


አባቱም እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፤ የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ነው።


ይህ ወንድምህ ግን ሞቶ ነበር፤ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶ ነበር፤ አሁን ተገኘ፤ ስለዚህ በጣም ልንደሰት ይገባናል።’ ”


“ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ ሲል በልቡ ጸለየ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኔ እንደ ሌሎች ሰዎች ቀማኛ፥ ግፈኛ አመንዝራ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ፤ ይልቁንም እንደዚህ እንደ ቀራጭ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios