Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 11:54 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 ይህንንም ያደረጉት በንግግሩ ሊያጠምዱት ፈልገው ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 ከአፉ በሚወጣውም ቃል ሊያጠምዱት ያደቡ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 በዚህም እርሱ ከሚናገረው አንድ ነገርን ለማጥመድ አደቡበት።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 በአ​ነ​ጋ​ገ​ሩም ሊያ​ስ​ቱ​ትና ሊያ​ጣ​ሉት ያደ​ቡ​በት ነበር።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 11:54
12 Referências Cruzadas  

የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቊጣ ልብሱን ቀደደ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ “የሶርያ ንጉሥ ይህን ሰው እንደምፈውስለት አድርጎ እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከቈዳ በሽታ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? በእርግጥ ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ መፈለጉን በግልጥ ያሳያል!” አለ።


ከዚህ በኋላ ፈሪሳውያን ሄዱና እንዴት አድርገው ኢየሱስን በንግግሩ እንደሚያጠምዱት ተማከሩ፤


ኢየሱስ ግን ክፋታቸውን ዐውቆ፥ “እናንተ ግብዞች! ስለምን ትፈትኑኛላችሁ?


ከእነርሱም አንድ የሕግ መምህር፥ ኢየሱስን ሊፈትነው ፈልጎ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦


ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑ አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስን በንግግሩ ለማጥመድ ወደ እርሱ ተላኩ።


ኢየሱስን ሊከሱት የፈለጉ ሰዎች፥ “እስቲ በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደ ሆነ እንይ!” ብለው ይጠባበቁት ነበር።


ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ሊሄድ በተነሣ ጊዜ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ይቃወሙትና ብዙ ጥያቄም ያቀርቡለት ጀመር፤


ስለዚህ ኢየሱስን ለመያዝ ምቹ ጊዜ ይጠብቁ ነበር። ለገዥው ሥልጣንና ፍርድ አሳልፈው ለመስጠት የሚያስችላቸውን የወንጀል ቃል ከእርሱ ለማግኘት ይፈልጉ ነበር፤ ስለዚህ ቅን ሰዎች መስለው፥ በንግግሩ የሚያጠምዱትን ሰላዮች ላኩበት።


እነርሱም በሕዝቡ ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም፤ ስለዚህ በመልሱ ተደንቀው ዝም አሉ።


ነገር ግን እሺ አትበላቸው፤ እርሱን ሳንገድል እህል አንበላም፤ ውሃም አንጠጣም በማለት የተማማሉ ከአርባ የሚበልጡ ሰዎች እርሱን ለመግደል አድፍጠዋል፤ አሁን እነርሱ የሚጠብቁት የአንተን መልስ ብቻ ነው።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios