Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 14:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፥ ከዚህም ጋር የእህል መባ ያቅርብ፤ ካህኑም ለሚነጻው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያስተስርይለት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከእነዚህም አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ከእህሉ ቍርባን ጋራ ያቅርብ፤ በዚህም ሁኔታ ካህኑ ለሚነጻው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ከእህል ቁርባን ጋር ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፥ ካህኑም ለሚነጻው ሰው በጌታ ፊት ያስተሰርይለታል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ሌላ​ዪ​ቱ​ንም ከእ​ህል ቍር​ባን ጋር ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ለሚ​ነ​ጻው ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እንደሚቻለው አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ከእህል ቍርባን ጋር ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል ካህኑም ለሚነጻው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 14:31
5 Referências Cruzadas  

በእጁ መዳፍ ላይ የተረፈውንም ዘይት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፍስሰው፤ በዚህም ዐይነት ካህኑ በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል።


የሚነጻውም ሰው ከዋኖስ ወይም ከርግብ እርሱ የሚችለውን አንዱን ያቅርብ፤


ከሥጋ ደዌ በሽታ ለመንጻት የተመደበውን መሥዋዕት በድኽነቱ ምክንያት ማቅረብ ለማይችል ሰው የሚፈጸመው ሥርዓት ይህ ነው።”


ካህኑም ከእነርሱ አንዱን ኃጢአት የሚሰረይበት መሥዋዕት፥ ሌላውንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፤ ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል።


“አንድ ሰው በግ ወይም ፍየል ማቅረብ ካልቻለ ግን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንደኛይቱን ስለ ኀጢአት ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሁለተኛይቱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ የበደሉን ዕዳ ይከፍል ዘንድ ለእግዚአብሔር ያምጣ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios