Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 13:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ቊስሉ ያለበትም ቦታ እየሰፋ መሄዱ ከታወቀ፥ ያ የሥጋ ደዌ ስለ ሆነ ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በቈዳው ላይ ተስፋፍቶ ካገኘውም፣ ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ፤ የሚተላለፍ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በቆዳውም ላይ ቢስፋፋ፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ደዌ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በቆ​ዳ​ውም ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነው፤ በእ​ት​ራቱ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በቁርበቱም ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ደዌ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 13:22
4 Referências Cruzadas  

“ማንም ሰው በሰውነቱ ላይ እባጭ ወይም ሽፍታ ወይም ቋቊቻ ቢታይና በገላው ላይ የሥጋ ደዌ ቢመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ከልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት።


ነገር ግን ካህኑ መርምሮት በቈዳው ላይ ያለው ጠጒር ወደ ነጭነት ባይለወጥና ከሌላው የሰውነቱ ቆዳ ይበልጥ ጐድጒዶ ባይገኝ፥ የቀለሙ ልዩነት ስለ ተቀነሰ ካህኑ ያን ሰው ለሰባት ቀን በቤት ውስጥ ተዘግቶበት እንዲቈይ ያድርግ፤


ነገር ግን ቋቁቻው ምንም ለውጥ ሳያደርግና ሳይስፋፋ ቢገኝ የእባጭ ጠባሳ መሆኑ ታውቆ መንጻቱን ካህኑ ያስታውቅለት።


በሰባተኛው ቀን ተመልሶ መጥቶ እንደገና ይመርምረው፤ የሻጋታው ምልክት ተስፋፍቶ ቢገኝ፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios