Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 22:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ከዚህም በኋላ የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና መሪዎቹ በገለዓድ ከሚገኙት ከሮቤልና ከጋድ ሕዝቦች ዘንድ በከነዓን ምድር ወደሚገኙት ወደ እስራኤል ሕዝብ ተመልሰው በመምጣት፥ ያገኙትን ማስረጃ አቀረቡ፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ከዚያም የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና መሪዎቹ፣ ከሮቤልና ከጋድ ወገኖች ጋራ በገለዓድ ምድር ከተነጋገሩ በኋላ፣ ወደ ከነዓን ተመልሰው፣ ሁኔታውን ለእስራኤላውያን ነገሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና አለቆቹ ከሮቤል ልጆችና ከጋድ ልጆች ዘንድ ከገለዓድ አገር ወደ ከነዓን አገር ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ ወሬም ይዘውላቸው መጡ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 የካ​ህ​ኑም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ከእ​ር​ሱም ጋር የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች ከሮ​ቤል ልጆ​ችና ከጋድ ልጆች፥ ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ዘንድ ከገ​ለ​ዓድ ሀገር ወደ ከነ​ዓን ሀገር ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ ወሬም አመ​ጡ​ላ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና አለቆቹ ከሮቤል ልጆችና ከጋድ ልጆች ዘንድ ከገለዓድ አገር ወደ ከነዓን አገር ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ ወሬም አመጡላቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 22:32
4 Referências Cruzadas  

ቀዝቃዛ ውሃ በሙቀት ጊዜ የሚያረካውን ያኽል ታማኝ መልእክተኛም የላከውን ሰው ያረካል።


ስለዚህም የአልዓዛር ልጅ ካህኑ ፊንሐስ እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን ዐወቅን፤ እናንተ በእርሱ ላይ አላመፃችሁም፤ ስለዚህም የእስራኤልን ሕዝብ ከእግዚአብሔር ቅጣት አድናችኋል።”


እስራኤላውያንም በመልሱ ረክተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም በኋላ የሮቤልና የጋድ ሕዝብ የሚኖሩባትን ምድር ለመደምሰስ ጦርነት ስለ ማንሣት ጉዳይ መናገር አልፈለጉም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios