Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 22:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከፊንሐስም ጋር ዐሥር ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህም እያንዳንዱ በምዕራብ ከሚገኙት ነገዶች የተውጣጡ በየጐሣቸው የቤተሰብ መሪዎች ናቸው፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከርሱም ጋራ እያንዳንዱን የእስራኤልን ነገድ የሚወክሉ ዐሥር አለቆች ዐብረው ላኩ፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው ከእስራኤላውያን ጐሣዎች የተውጣጡ የየቤተ ሰቡ አለቆች ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከእርሱም ጋር ዐሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ፤እንያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቆች ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ዐሥር አለ​ቆ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ አንድ አንድ የእ​የ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አለቃ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በእ​ስ​ራ​ኤል አእ​ላ​ፋት መካ​ከል የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አለቃ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከእርሱም ጋር አሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ፥ እንያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቃ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 22:14
3 Referências Cruzadas  

ከእስራኤላውያንም ሁሉ መካከል ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ እነርሱንም የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርጎ በሕዝቡ ላይ ሾማቸው።


ከእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ የቤተሰብ አለቃ ከእናንተ ጋር ይሁን።


እነርሱም የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ የሚኖሩት የምናሴ ሕዝብ ወደሚኖሩባት ወደ ገለዓድ ምድር መጥተው እንዲህ አሉአቸው፦


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios