Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 21:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 በእስራኤላውያን ይዞታ ሥር የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ከግጦሽ መሬታቸው ጋር አርባ ስምንት ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 እንግዲህ እስራኤላውያን ርስት አድርገው ከያዙት ምድር ለሌዋውያኑ የተሰጧቸው ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው በአጠቃላይ አርባ ስምንት ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰማሪያቸው ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት መካ​ከል የነ​በ​ሩት የሌ​ዋ​ው​ያን ከተ​ሞች ሁሉ በእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች ዙሪያ ካሉ ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር አርባ ስም​ንት ከተ​ሞች ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰምርያቸው ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 21:41
7 Referências Cruzadas  

እጅግ አስፈሪ የሆነ ቊጣቸው፥ እጅግ ጨካኝ የሆነ መዓታቸው፥ የተረገመ ይሁን። በእስራኤል ምድር ሁሉ እበታትናቸዋለሁ፤ በሕዝቡም መካከል እከፋፍላቸዋለሁ።


በዚህም ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ ሌዋውያን የሚኖሩባቸውን ከተሞች መደቡላቸው፤ ይህም በየከተማው ዙሪያ ያለውን የግጦሽ ቦታ ያጠቃልላል።


ሥርዓትህን ለያዕቆብ፥ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፤ በፊትህ ዕጣን ያጥናሉ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም በመሠዊያህ ላይ ያቀርባሉ።


ስለዚህም በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት የእስራኤል ሕዝብ ለሌዋውያን የሚከተሉትን ከተሞችና ለከብት ግጦሽ የሚሆን መሬት ከርስቶቻቸው ከፍለው ሰጡአቸው።


የሌዋውያን ነገድ ለሆኑት ለቀሪዎቹ የሜራሪ ጐሣዎች የተሰጡት ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው።


በእነዚህም መሬቶች በእያንዳንዱ ዘሪያ የግጦሽ መሬት ነበራቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios