Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 41:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በአፍንጫው መሰነጊያ አስገብተህ መንጋጋውንም በመንጠቆ ወግተህ ልትይዘው ትችላለህን?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 መሰነጊያ በአፍንጫው ልታስገባ፣ ወይም ጕንጩን በሜንጦ ልትበሳ ትችላለህን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ማንም ሊቀሰቅሰው የሚደፍር የለም፥ እንግዲህ በፊቴ መቆም የሚችል ማን ነው?

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የሚ​ከ​ራ​ከ​ረ​ኝና በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ርስ ማን ነው? ከሰ​ማይ በታች ያለ​ውም ሁሉ የእኔ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ያንቀሳቅሰውም ዘንድ የሚደፍር የለም፥ እንግዲህ በፊቴ መቆም የሚችል ማን ነው?

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 41:2
7 Referências Cruzadas  

በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”


ምሕረት እንድታደርግለት ይለምንሃልን? በመልካም አነጋገር ይለምንሃልን?


እግዚአብሔር ጠቢብና ኀያል ነው፤ ማነው እርሱን ተቋቊሞ ያልተሸነፈ?


ሰው በጥበቡ፥ በአስተዋይነቱና በዕቅዱ በእግዚአብሔር ላይ መነሣት አይችልም።


በዚያን ቀን እግዚአብሔር በጽኑ፥ በታላቁና በኀያል ሰይፉ የሚስለከለከውንና የሚጠመጠመውን እባብ ሌዋታንን ይቀጣል፤ የባሕሩንም ዘንዶ ይገድላል።


በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios