Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ፈጽሞ ከድተውኛል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት፣ ፈጽመው ከድተውኛል፤” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ አታለዋል ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ ወን​ጅ​ለ​ዋል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ ወንጅለዋል ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 5:11
9 Referências Cruzadas  

“ለጻድቁ ለእርሱ ክብር ይሁን!” የሚል መዝሙር ከዓለም ዳርቻ ይሰማል። እኔ ግን እጅግ በመክሳት ስለ መነመንኩ ወዮልኝ! ከዳተኞች በከዳተኝነታቸው ጸንተዋል፤ ከዳተኛነታቸውም እየባሰ ሄዶአል።


እኔ የምናገረውን አትሰሙም፤ ለማወቅም አትፈልጉም፤ ከጥንት ጀምሮ ጆሮአችሁ የተደፈነ ነው፤ ይህም የሆነው እናንተ በጣም ከዳተኞች መሆናችሁንና ከተወለዳችሁ ጀምሮ ዐመፀኞች ተብላችሁ መጠራታችሁን ዐውቃለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! ከአንተ ጋር በምከራከርበት ጊዜ ሁሉ አንተ ትክክለኛ ነህ፤ አሁን ግን ስለ ትክክለኛ ፍርድ ጥያቄ አለኝ፤ የኃጢአተኛ ሕይወት የተቃና የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? አታላዮችስ ሁሉ ነገር የሚሳካላቸው ስለምንድን ነው?


አንቺ ግን ባልዋን እንደ ከዳች ሚስት ለእኔ ታማኝ አልሆንሽም፤ ይህን እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።”


የሕዝቤን የወይን ተክል ቈራርጠው የሚያበላሹ ጠላቶችን እልካለሁ፤ ነገር ግን ሥር መሠረታቸውን እንዲያጠፉ አላደርግም፤ ቅርንጫፎቹ የእኔ ባለመሆናቸው፥ ቈርጠው እንዲጥሉአቸው አዛለሁ።


ሕዝቤ እምነተ ቢሶችና አታላዮች ስለ ሆኑ፥ ከእነርሱ ተለይቼ በምድረ በዳ ውስጥ የምኖርበት የመንገደኞች ማደሪያ ቦታ ባገኝ፥ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር!


እነርሱ ራሳቸው ጣዖት አምላኪዎች ስለ ሆኑ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልተገኙም። ልጆቻቸውም እንደ ጣዖት ልጆች ተቆጥረዋል፤ ስለዚህ በዚህ ወር መባቻ እነርሱም ምድራቸውም አብረው ይጠፋሉ።


“እነርሱ ወደ አገሪቱ በገቡ ጊዜ ‘አዳም’ በምትባል ቦታ ከእኔ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፈረሱ፤ ለእኔ የማይታመኑ መሆናቸውንም ገለጡ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios