Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 44:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 “አሁንም ብላቴናው ከእኛ ተለይቶ በመቅረት ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ ብንመለስ የብላቴናው ነፍስ ከእርሱ ጋር የታሰረች ስለ ሆነ፥

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 “እንግዲህ አሁን ልጁን ሳንይዝ ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ ብመለስ፣ ሕይወቱ ከልጁ ሕይወት ጋራ በጥብቅ የተሳሰረ ስለ ሆነ፣

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 እንግዲህ አሁን ልጁን ሳንይዝ ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ ብመለስ፥ ሕይወቱ ከልጁ ሕይወት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ስለ ሆነ፥

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 አሁ​ንም እኛ ወደ አባ​ታ​ችን ወደ አገ​ል​ጋ​ይህ ብን​ሄድ፥ ብላ​ቴ​ና​ውም ከእኛ ጋር ከሌለ፥ ነፍሱ በብ​ላ​ቴ​ናው ነፍስ ታስ​ራ​ለ​ችና

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 አሁንም እኔ ወደ አባቴ ወደ ባሪያህ ብሄድ ብላቴናውም ከእኛ ጋር ከሌለ ነፍሱ በብላቴናው ነፍስ ታስራለችና ብላቴናው ለእን ጋር እንደሌለ ባየ ጊዜ ይሞታል

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 44:30
8 Referências Cruzadas  

ዮሴፍም “ይህንንስ ከቶ አላደርገውም! ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ የእኔ ባሪያ መሆን አለበት፤ ሌሎቻችሁ በሰላም ወደ አባታችሁ መመለስ ትችላላችሁ!” አለ።


እኛም ‘ሽማግሌ አባት አለን፤ በስተርጅና የወለደውም ታናሽ ወንድም አለን፤ የልጁ ወንድም ሞቶአል፤ ከእናቱ ልጆች የቀረው እርሱ ብቻ ስለ ሆነ አባቱ በጣም ይወደዋል’ ብለንህ ነበር፤


እኛም ‘ልጁ አባቱን ትቶ መምጣት አይችልም፤ ትቶ ከመጣ ግን አባትየው መሞቱ የማይቀር ነው’ ብለን ለአንተ ለጌታችን ነግረንህ ነበር።


ብላቴናው ከእኛ ጋር እንደሌለ ሲያይ ይሞታል፤ እኛ አገልጋዮችህም የአገልጋይህን የአባታችንን ሽበት በሐዘን ወደ መቃብር እናወርዳለን፤


ልጁን ሳልይዝ እንዴት ወደ አባቴ መመለስ እችላለሁ? ይህን የመሰለ ከባድ ሥቃይ በአባቴ ላይ ሲደርስ ማየት አልችልም።”


ንጉሡም እጅግ አዘነ፤ በቅጽር በሩ አናት ላይ ወደሚገኘውም ክፍል ወጥቶ አለቀሰ፤ ወደዚያም ሲመጣ “ልጄ ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! አቤሴሎም ልጄ! ምነው በአንተ ምትክ እኔ በሞትኩ ልጄ ሆይ! አቤሴሎም ልጄ!” እያለ በመጮኽ ያለቅስ ነበር።


ሳኦልና ዳዊት ንግግራቸውን ከጨረሱ በኋላ የሳኦል ልጅ ዮናታን ከዳዊት ጋር እጅግ የተቀራረበ አንድነት መሠረተ፤ እንደ ራሱም አድርጎ ወደደው፤


ማንም ሰው በአንተ ላይ አደጋ ጥሎ ሊገድልህ ቢፈልግ አንድ ሰው ውድ የሆነ ሀብቱን እንደሚጠብቅ አምላክህ እግዚአብሔር አንተን በሰላም ይጠብቅሃል፤ ስለ ጠላቶችህም የሆነ እንደ ሆነ አንድ ሰው ድንጋዩን ከወንጭፍ እንደሚያስፈነጥር እግዚአብሔር ራሱ አሽቀንጥሮ ይጥላቸዋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios