Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 44:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ወንድማማቾቹ ይህን ባዩ ጊዜ በሐዘን ልብሶቻቸውን ቀደዱ፤ ስልቻዎቻቸውንም ጭነው ወደ ከተማ ተመለሱ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን በሐዘን ቀደዱ፤ ሁሉም ስልቾቻቸውን በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማዪቱ ተመለሱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን በኀዘን ቀደዱ፤ ሁሉም ስልቾቻቸውን በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማዪቱ ተመለሱ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ቀደዱ፤ ዓይ​በ​ታ​ቸ​ው​ንም በየ​አ​ህ​ዮ​ቻ​ቸው ጭነው ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ተመ​ለሱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ልብሳቸውንም ቀደዱ ዓይበታቸውንም በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማይቱ ተመለሱ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 44:13
7 Referências Cruzadas  

ከከተማው ወጥተው ገና ጥቂት መንገድ ርቀው እንደ ሄዱ፥ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፤ “እነዚያን ሰዎች ተከታትለህ ያዛቸው፤ ወደ እነርሱም ስትደርስ ‘በመልካም ፈንታ ክፉ የመለሳችሁት ስለምንድን ነው?


ዳዊትም በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩ ተከታዮቹ ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ፤


በሦስተኛው ቀን አንድ ወጣት ከሳኦል ሰፈር መጣ፤ ልብሱን ቀዶ በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር፤ ወደ ዳዊትም ቀርቦ በአክብሮት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤


እዚያም እንደ ደረሰች አዲሱ ንጉሥ በተለመደው ባህል መሠረት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሚገኘው ዐምድ አጠገብ ቆሞ አየችው፤ እርሱም በጦር አዛዦችና በእምቢልታ ነፊዎች ታጅቦ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ በደስታ ተሞልተው እልል እያሉ እምቢልታ ይነፉ ነበር፤ ዐታልያም በድንጋጤ ልብስዋን ቀዳ “ይህ በክሕደት የተፈጸመ ሤራ ነው! ሤራ ነው!” ስትል ጮኸች።


ምድሪቱን እንዲያጠኑ ከተላኩት ሰዎች ሁለቱ የነዌ ልጅ ኢያሱና የየፉኔ ልጅ ካሌብ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios