Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 31:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ስለዚህ እኔና አንተ በመሐላ የስምምነት ውል እናድርግ፤ ለምናደርገው ውል ምስክር ሆኖ እንዲኖር ድንጋይ ሰብስበን በመከመር ሐውልት እናቁም።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 በል አሁን ቃል ኪዳን እንጋባ፤ ኪዳኑም በአንተና በእኔ መካከል ምስክር ይሁን።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 አሁንም ና፥ አንተና እኔ ቃል ኪዳን እንጋባ፥ በእኔና በአንተ መካከልም ምስክር ይሁን።”

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 አሁ​ንም ና፤ አን​ተና እኔ ቃል ኪዳን እን​ጋባ፤ በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ይሁን።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 አሁንም ና አንተና እኔ ቃል ኪዳን እንጋባ በእኔና በአንተ መካከልም ምስክር ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 31:44
11 Referências Cruzadas  

በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤


ላባም “እነሆ፥ ዛሬ ይህ የድንጋይ ካብ በእኔና በአንተ መካከል ምስክር ነው” አለ። ገለዓድ ተብላ የተጠራችበት ምክንያት ለዚህ ነው።


እኔ አንተን ለማጥቃት ይህን የድንጋይ ቊልል እንደማላልፍ፥ አንተም እኔን ለማጥቃት ይህን የድንጋይ ቊልልና ይህን የመታሰቢያ ሐውልት እንደማታልፍ፥ ይህ የድንጋይ ቊልልና ይህ የመታሰቢያ ሐውልት ምስክሮች ናቸው።


“ይህን መዝሙር ጽፈህ ለእስራኤላውያን አስተምራቸውና እንዲዘምሩት አድርግ፤ ይህም መዝሙር በእነርሱ ላይ ማስረጃ ይሆንልኛል።


ብዙ ከባድ ችግሮች ሲደርሱባቸው ይህ በልጆቻቸው የማይረሳ መዝሙር ሲዘመር ምስክር ይሆንባቸዋል። በመሐላ ቃል ወደገባሁላቸው ምድር ከማስገባቴ በፊት አሁን እንኳ ምን ዐይነት ዝንባሌ እንዳላቸው ዐውቃለሁ።”


“የእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈበትን ይህን መጽሐፍ ወስዳችሁ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አኑሩት፤ በዚህም ዐይነት በሕዝቡ ላይ ምስክር ይሆንባቸዋል።


እኛ እርሱን የሠራነው በእኛና በእናንተ ሕዝብ መካከል ምልክት ሆኖ እንዲኖር ነው፤ ይኸውም ከእኛ በኋላ ለሚነሡት ትውልዶች በተቀደሰ ድንኳኑ ፊት እግዚአብሔርን እንደምናመልክ የሚቃጠልና ሌላም መሥዋዕት፥ እንዲሁም የአንድነት መሥዋዕት ስናቀርብ ለመኖራችን ምስክር ይሆናል፤ ይኸውም የእናንተ ዘሮች የእኛን ልጆች ‘ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት የላችሁም’ እንዳይሉአቸው ለማድረግ ይጠቅማል፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios