Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 31:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ከአንተ ጋር የነበርኩበትን ኻያ ዓመት ያሳለፍኩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ከዚህም ዐሥራ አራቱን ዓመት ያገለገልኩህ ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ለማግኘት ብዬ ነው፤ የቀሩትን ስድስት ዓመቶች ያገለገልኩህ መንጋዎችህን ለማግኘት ብዬ ነው። ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋወጥክብኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ሃያ ዓመት በቤትህ የኖርሁት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ዐሥራ አራት ዓመት ለሁለቱ ልጆችህ ብዬ አገለገልሁ፤ ስድስት ዓመት ስለ መንጋዎችህ ስል አገለገልሁ፤ ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋውጠህብኛል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 እነዚህን ሃያ ዓመታት በአንተ ቤት ነበርሁ፥ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆችህ፥ ስድስት ዓመትም ስለ በጎችህ ተገዛሁልህ፥ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለዋወጥኸው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ለአ​ንተ ቤት የተ​ገ​ዛ​ሁ​ልህ ዛሬ ሃያ አንድ ዓመት ነው፤ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆ​ችህ፥ ሰባት ዓመት ስለ በጎ​ችህ ተገ​ዛ​ሁ​ልህ፤ ደመ​ወ​ዜ​ንም ዐሥር ጊዜ ለዋ​ወ​ጥ​ኸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እንዲሁ በአንተ ቤት ሀያ ዓመት ነበርሁ አሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆችህ ስድስት ዓመትም ስለ በጎችህ ተገዛሁልህ፤ ደመወዜንም አሥር ጊዜ ለዋወጥኸው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 31:41
12 Referências Cruzadas  

የወንድምህ ቊጣ እስኪበርድ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እዚያው ቈይ፤


ላባ ያዕቆብን “ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነጻ ልታገለግለኝ አይገባህም፤ ስለዚህ ምን ያኽል ደመወዝ ላስብልህ?” አለው።


የምትፈልገውን ደመወዝ ልክ ንገረኝና እከፍልሃለሁ” አለው።


ከአንተ ጋር መኖር ከጀመርኩ ኻያ ዓመት ሆነኝ፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ በጎችህና ፍየሎችህ የጨነገፉበት ጊዜ የለም፤ ከመንጋህም አንድ ጠቦት እንኳ በልቼ አላውቅም፤


ብዙ ጊዜ በቀን ሐሩርና በሌሊት ቅዝቃዜ እሠቃይ ነበር፤ በቂ እንቅልፍ ያገኘሁበት ጊዜ አልነበረም።


ጒልበቴን ሳልቈጥብ በትጋት አባታችሁን እንዳገለገልኩ እናንተም ታውቃላችሁ፤


እርሱ ግን ዐሥር ጊዜ ደመወዜን በመለዋወጥ አታለለኝ፤ ሆኖም እኔን ለመጒዳት እግዚአብሔር አልፈቀደለትም፤


እንዲህም በማለት አዘዛቸው፥ “ለጌታዬ ለዔሳው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ ‘ታማኝ አገልጋይህ እኔ ያዕቆብ እስከ አሁን የቈየሁት ከላባ ጋር እንደ ነበር ልነግርህ እወዳለሁ፤


ነገር ግን እኔ አሁን የሆንኩትን ሆኜ የምገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው፤ የተሰጠኝም ጸጋ ያለ ፍሬ አልቀረም፤ እንዲያውም ከሌሎቹ ይበልጥ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።


በጒዞዬ ብዛት የወንዝና የጐርፍ፥ የሽፍቶችም አደጋ ደርሶብኛል፤ ከአይሁድ ወገኖቼና ከአሕዛብ አደጋ ደርሶብኛል፤ በከተማና በበረሓ በባሕርም አደጋ ደርሶብኛል፤ እንዲሁም ከሐሰተኞች አማኞች አደጋ ደርሶብኛል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios