Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 31:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ከዘመዶቹ ጋር ሆኖ ያዕቆብን ተከታተለው፤ ሰባት ቀን ከተጓዘ በኋላ ገለዓድ በተባለው ተራራማ አገር ላይ ሊደርስበት ተቃረበ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ላባ ዘመዶቹን ይዞ ተነሣ፤ ያዕቆብንም ሰባት ቀን ተከታትሎ ገለዓድ በተባለ ኰረብታማ አገር ደረሰበት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ከዘመዶቹም ጋር ሆኖ የሰባት ቀን መንገድ ያህል ተከተለው፥ ከዚያም በገለዓድ ተራራማ አገር ላይ አገኛቸው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ላባም ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ ይዞ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ተከ​ተ​ላ​ቸው፤ በገ​ለ​ዓድ ተራ​ራም ላይ አገ​ኛ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ከወንድሞቹም ጋር ሆኖ የሰባት ቀን መንገድ ያህል ተከተለው በገለዓድ ተራራም ላይ ደረሰበት

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 31:23
6 Referências Cruzadas  

ከዚህ በኋላ አብራም ሎጥን እንዲህ አለው፤ “እኛ ወንድማማች ስለ ሆንን በእኔና በአንተ መካከል እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ጠብ ሊነሣ አይገባም፤


“ለጌታዬ ያለውን ታማኝነትና ዘለዓለማዊ ፍቅር የጠበቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በቀጥታ መርቶ ወደ ጌታዬ ዘመዶች ቤት ያመጣኝ እርሱ ነው” አለ።


ያዕቆብ በስውር መሄዱን ላባ ከሦስት ቀን በኋላ ሰማ፤


በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ለላባ በሕልም ተገለጠለትና “ያዕቆብን፥ ክፉም ሆነ ደግ እንዳትናገረው ተጠንቀቅ” አለው።


ሙሴ ባደገ ጊዜ ወገኖቹን ለመጐብኘት ሄደ፤ ከባድ ሥራ መሥራታቸውን ተመለከተ፤ እንዲያውም አንድ ግብጻዊ ከወገኖቹ አንዱ የሆነውን ዕብራዊ ሲደበድብ አየ።


በማግስቱም ወደዚያው ስፍራ ተመልሶ ሲሄድ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አየ፤ በደል የሠራውንም ሰው ተመልክቶ “ወገንህ የሆነውን ዕብራዊ ለምን ትመታዋለህ?” ሲል ጠየቀው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios