Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 21:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 አብርሃምም “እነዚህን ሰባት ቄቦች ተቀበለኝ፤ እነርሱን ከተቀበልከኝ ይህን ጒድጓድ የቈፈርኩ እኔ መሆኔን ታረጋግጣለህ” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 አብርሃምም፣ “ይህን የውሃ ጕድጓድ የቈፈርሁ እኔ ለመሆኔ ምስክር እንዲሆን እነዚህን ሰባት እንስት በጎች ዕንካ ተቀበለኝ” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 እርሱም፦ እኔ ይህችን የውኃ ጉድጓድ እንደቆፈርሁ ምስክር ይሆንልኝ ዘንድ እነዚህን ሰባት ቄቦች በጎች ከእጄ ትወስዳለህ አለው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እር​ሱም፥ “እኔ ይህ​ችን የውኃ ጕድ​ጓድ እን​ደ​ቈ​ፈ​ርሁ ምስ​ክር ይሆ​ኑ​ልኝ ዘንድ እነ​ዚ​ህን ሰባ ቄቦች በጎች ከእጄ ትወ​ስ​ዳ​ለህ” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እርሱም፦ እኔ ይህችን የውኃ ጕድጓድ እንደቆፈርሁ ምስክር ይሆንልኝ ዘንድ እነዚህን ሰባት ቄቦች በጎች ከእጄ ትወስዳለህ አለው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 21:30
8 Referências Cruzadas  

በዚያን ጊዜ አብርሃም ሰባት ሴት በጎችን ከመንጋው ለየ፤


አቤሜሌክም “እነዚህን ሰባት ሴት በጎች ለይተህ ያቆምካቸው ለምንድን ነው?” አለው።


ስለዚህ የይስሐቅ አባት አብርሃም በሕይወት በነበረበት ዘመን የእርሱ አገልጋዮች ቆፍረዋቸው የነበሩትን የውሃ ጒድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው።


አብርሃም በሕይወት ሳለ አስቈፍሮአቸው የነበሩትንና አብርሃም ከሞተ በኋላ ግን ፍልስጥኤማውያን የደፈኑአቸውን የውሃ ጒድጓዶች ይስሐቅ እንደገና እንዲቈፈሩ አደረገ፤ አባቱ ባወጣላቸው ስሞችም ጠራቸው።


እኔ አንተን ለማጥቃት ይህን የድንጋይ ቊልል እንደማላልፍ፥ አንተም እኔን ለማጥቃት ይህን የድንጋይ ቊልልና ይህን የመታሰቢያ ሐውልት እንደማታልፍ፥ ይህ የድንጋይ ቊልልና ይህ የመታሰቢያ ሐውልት ምስክሮች ናቸው።


ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የነገረንን ቃል ሁሉ ስለ ሰማ ይህ ድንጋይ በእኛ ላይ ምስክር ነው፤ ስለዚህም አምላካችሁን ብትክዱ በእናንተ ላይ ምስክር ይሆንባችኋል።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios