Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መክብብ 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ጥበበኛው ጠቢብ ብቻ ሳይሆን ዕውቀትን ለሕዝቡ ማስተማር ቀጠለ፤ ብዙ ምሳሌዎችን መርምሮ ካጠና በኋላ በቅደም ተከተል አዘጋጀ፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሰባኪው ጥበበኛ ብቻ አልነበረም፤ ነገር ግን ለሕዝቡ ዕውቀትንም ያስተምር ነበር። እርሱም በጥልቅ ዐሰበ፤ ተመራመረም፤ ብዙ ምሳሌዎችንም በሥርዐት አዘጋጀ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሰባኪውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕዝቡ እውቀትን አስተማረ፥ እርሱም ብዙ ምሳሌዎችን መረመረና ፈላለገ አስማማም።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሰባ​ኪ​ውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕ​ዝቡ ዕው​ቀ​ትን አስ​ተ​ማረ፥ ጆሮ​ውም እን​ቆ​ቅ​ል​ሽን መረ​መረ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሰባኪውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕዝቡ እውቀትን አስተማረ፥ እርሱም ብዙ ምሳሌዎችን መረመረና ፈላለገ አስማማም።

Ver Capítulo Cópia de




መክብብ 12:9
8 Referências Cruzadas  

በፊትህ ሁልጊዜ በመገኘት ጥበብ የሞላበት ንግግርህን የሚሰሙ ሰዎችህና ባለሟሎችህ እንዴት የታደሉ ናቸው!


ሦስት ሺህ ምሳሌዎችንና አንድ ሺህ አምስት የመዝሙር ድርሰቶችን ደረሰ፤


እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከል ሰላም ስለ ነበረ ሁለቱም የጋራ ስምምነት ውል አደረጉ።


እነዚህ ምሳሌዎች የዳዊት ልጅ የሆነው፥ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን የተናገራቸው ናቸው።


እነዚህ የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው፤ ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።


እነዚህ ሌሎች የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው፤ እነርሱም በእጅ የተጻፉት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቤተ መንግሥት በነበሩ ሰዎች አማካይነት ነበር።


በዚያን ጊዜ ጠቢባን እንደ ሰማይ ብርሃን ያንጸባርቃሉ፤ ብዙ ሰዎችን በማስተማር ከክፉ መንገድ ወደ ደግ ሥራ የመለሱ ሁሉ ለዘለዓለም እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበራሉ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios