Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 30:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ቃሉ ለእናንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ትጠብቀውም ዘንድ በአፍህና በልብህ ውስጥ ይገኛል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ነገር ግን ቃሉ ለአንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ታደርገውም ዘንድ በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ነገር ግን ቃሉ ለአንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ታደርገውም ዘንድ በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ታደ​ር​ገው ዘንድ ቃሉ በአ​ፍ​ህና በል​ብህ፥ በእ​ጅ​ህም ውስጥ ለአ​ንተ እጅግ ቅርብ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ነገር ግን ታደርገው ዘንድ ቃሉ በአፍህና በልብህ ውስጥ ለአንተ እጅግ ቅርብ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 30:14
14 Referências Cruzadas  

አንተ ተክለሃቸዋል፤ እነርሱም ሥር ሰደዋል፤ አድገውም ፍሬ ያፈራሉ፤ በአፋቸው ያከብሩሃል፤ ልባቸው ግን ከአንተ የራቀ ነው።


እነዚያ ዐመፀኞች ቢሰሙህም ባይሰሙህም ነቢይ በመካከላቸው መኖሩን ያውቃሉ።


ስለዚህም ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሕዝቤ አንተ ምን እንደምትናገር ለማዳመጥ ብቻ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የምትነግራቸውን ሁሉ አይፈጽሙም፤ የምትናገረውን ቃል የሚወዱት መስለው ይታያሉ፤ ነገር ግን ከበዝባዥነታቸው አይመለሱም፤


ነገር ግን አንተ የተናገርካቸው ቃላት በእርግጥ ይፈጽማሉ፤ እውን ሆነው በሚፈጸሙበትም ጊዜ በመካከላቸው ነቢይ መኖሩን ያውቃሉ።”


‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም፤ ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚፈጽም ነው።


ሙሴን ብታምኑ ኖሮ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና እኔንም ባመናችሁ ነበር።


“እናንተ ከአብርሃም ዘር የተወለዳችሁ ወንድሞችና እናንተም እግዚአብሔርን የምትፈሩ አሕዛብ! ይህ የመዳን ቃል የተላከው ለእኛ ነው።


‘እርሱን ሰምተን እንታዘዘው ዘንድ ከባሕር ማዶ ተሻግሮ ማን ሊያመጣልን ይችላል?’ ብለህ እንዳትጠይቅ፥ እርሱ የሚገኘው ከባሕር ማዶ አይደለም።


“ዛሬ እኔ ሕይወትንና መልካምነትን ወይም ሞትንና ክፋትን እንድትመርጥ ሰጥቼሃለሁ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios