Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 1:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 “ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለሁላችንም እንዲህ አለ፤ ‘በጠላቶቻችን ይማረካሉ ያላችኋቸው ሕፃናትና ክፉና ደጉን ለይተው የማያውቁ ልጆቻችሁ ብቻ ወደዚያች ምድር ይገባሉ፤ ምድሪቱን ለእነርሱ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ይወርሱአታል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ይማረካሉ ያላችኋቸው ታናናሾች፣ ክፉና በጎውን ለይተው የማያውቁት ልጆቻችሁ ምድሪቱን ይገቡባታል፤ ለእነርሱም እሰጣቸዋለሁ፤ እነርሱም ይወርሷታል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 “ደግሞ፦ ‘ይማረካሉ ያላችኋቸው ሕፃናቶቻችሁ፥ ዛሬም መልካሙን ከክፉ መለየት የማይችሉ ልጆቻችሁ፥ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ፥ ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ፥ ይወርሱአታልም።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ደግሞ፦ ይማ​ረ​ካሉ ያላ​ች​ኋ​ቸው ልጆ​ቻ​ችሁ፥ ዛሬም መል​ካ​ሙን ከክፉ መለ​የት የማ​ይ​ችሉ ሕፃ​ኖ​ቻ​ችሁ እነ​ርሱ ወደ​ዚያ ይገ​ባሉ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ለእ​ነ​ርሱ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ይወ​ር​ሱ​አ​ታ​ልም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ደግሞ፦ ለምርኮ ይሆናሉ ያላችኋቸው ሕፃናቶቻችሁ፥ ዛሬም መልካሙን ከክፉ መለየት የማይችሉ ልጆቻችሁ፥ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ፥ ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ ይወርሱአታልም።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 1:39
7 Referências Cruzadas  

ነነዌ ክፉና ደጉን የማይለዩ ከአንድ መቶ ኻያ ሺህ ሕዝብ በላይ የሚኖሩባት ከተማ ነች፤ ብዙ እንስሶችም አሉባት፤ ታዲያ እኔ ለዚህች ታላቂቱ ከተማ አልራራምን?”


እግዚአብሔር ወደዚያች ምድር የሚወስደን ለምንድን ነው? እኛ ሁላችን በጦርነት እናልቃለን፤ ሚስቶቻችንና ልጆቻችንም ይማረካሉ፤ ወደ ግብጽ ብንመለስ መልካም አይሆንምን?”


ልጆቻችን ምርኮኞች ሆነው ይቀራሉ ብላችሁ የተናገራችሁባቸውን እነርሱን እናንተ ወደናቃችኋት ምድር አገባቸዋለሁ፤ ርስታቸውም ትሆናለች።


የእግዚአብሔር ምርጫ በሥራ ሳይሆን በጥሪ መሆኑን ለመግለጥ ሁለቱ ልጆች ከመወለዳቸውና ክፉም ሆነ ደግ ከማድረጋቸው በፊት


እኛም ሁላችን ከዚህ በፊት በእነርሱ መካከል የሥጋችንን ፈቃድና የአእምሮአችንን ሐሳብ እየተከተልን በሥጋችን ምኞት እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም በተፈጥሮአችን በእግዚአብሔር ቊጣ ሥር ነበርን።


ኢያሱ የገረዛቸው እግዚአብሔር በእነርሱ ቦታ ያስነሣቸውን ልጆቻቸውን ነው፤ እነርሱ በጉዞ ላይ በነበሩ ጊዜ ስላልተገረዙ ሸለፈታሞች ነበሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios