Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




አሞጽ 6:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህ ተማርካችሁ በመሄድ እናንተ የመጀመሪያዎቹ ትሆናላችሁ፤ በዚያን ጊዜ የዚያ የቅጥ ያጣ ፈንጠዝያ ኑሮአችሁ ፍጻሜ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህ እናንተ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱት መካከል ናችሁ፤ መፈንጠዛችሁና መዝናናታችሁም ያበቃል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህ በመጀመሪያ ተማርከው ከሚፈልሱት ይሆናሉ፥ እንደ ፈቃዳቸው ከሚሆኑ መካከል ፈንጠዝያ ይርቃል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ስለ​ዚህ ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው አስ​ቀ​ድ​መው ይማ​ረ​ካሉ፤ ሯጮች የሚ​ሆኑ የኤ​ፍ​ሬም ፈረ​ሶ​ችም ያል​ቃሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ስለዚህ በምርኮ መጀመሪያ ይማረካሉ፥ ተደላድለው ከተቀመጡትም ዘንድ ዘፈን ይርቃል።

Ver Capítulo Cópia de




አሞጽ 6:7
17 Referências Cruzadas  

ራሴን ያዞረኛል፤ ከፍርሃት የተነሣም እንቀጠቀጣለሁ፤ ቀኑ ቶሎ እንዲመሽልኝ ተመኘሁ፤ ተስፋ ያደረግኹት ጭላንጭል አስደንጋጭ ሆነብኝ፦


የሚያስደስት የመሰንቆ፥ ሙዚቃና የአታሞ ድምፅ መሰማቱ ቀርቶአል፤ የበዓል አከባበር ሁሉ ቆሞአል።


በዚያኑ ሌሊት የባቢሎን ንጉሥ ብልጣሶር ተገደለ፤


እያንዳንዳችሁ በአቅራቢያችሁ በሚገኘው መሹለኪያ ቀዳዳ ተጐትታችሁ በመውጣት ወደ ሃርሞን ትጣላላችሁ።”


ከደማስቆ ወዲያ ርቃችሁ እንድትሰደዱ አደርጋለሁ።” ይህን የተናገርኩ እኔ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነኝ።


ወደ ቤርሳቤህ አትሂዱ፤ ቤቴል ፈራርሳ እንዳልነበረች ስለምትሆን በጌልገላ የሚኖሩ ሕዝቦችም ስደት ስለ ተፈረደባቸው ወደ ቤቴልም ሆነ ወደ ጌልጌላ አትሂዱ።”


እርሱም ‘ኢዮርብዓም በጦርነት ይሞታል፤ የእስራኤልም ሕዝብ ከሀገራቸው ተማርከው ይሄዳሉ’ ይላል።”


ስለዚህም አሜስያስ ሆይ! እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ ‘ሚስትህ በከተማይቱ አመንዝራ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በጦርነት ይሞታሉ፤ ርስትህንም ባዕዳን በገመድ ለክተው ይከፋፈሉታል፤ አንተም በአሕዛብ ምድር ትሞታለህ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ያለ ጥርጥር ተማርከው ከአገራቸው ይወሰዳሉ።’ ”


እናንተ ሰካራሞች! እርስ በርሱ የተያያዘ እሾኽና ድርቆሽ በእሳት ተቃጥሎ እንደሚጠፋ፥ እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።


ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”


ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትወልዳለህ፤ ነገር ግን የጦር ምርኮኞች ሆነው ስለሚወሰዱ ታጣቸዋለህ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios