Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 27:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ “የሰሜናዊ ምሥራቅ ዐውሎ ነፋስ” የሚባል ኀይለኛ ነፋስ ከደሴቲቱ ተነሥቶ ወደ ባሕሩ መጣባቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ብዙም ሳይቈይ ግን፣ “ሰሜናዊ ምሥራቅ” የሚሉት ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ከደሴቲቱ ተነሥቶ ቍልቍል መጣባቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ነገር ግን እጅግ ሳይዘገይ አውራቂስ የሚሉት ዓውሎ ነፋስ ከዚያ ወረደባቸው፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከጥ​ቂት ጊዜ በኋ​ላም አው​ራ​ቂስ የሚ​ሉት ጽኑዕ ዓውሎ ነፋስ መጣ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ነገር ግን እጅግ ሳይዘገይ አውራቂስ የሚሉት ዓውሎ ነፋስ ከዚያ ወረደባቸው፤

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 27:14
7 Referências Cruzadas  

ቀዛፊዎችሽ አውጥተው ወደ ጥልቁ ባሕር ወሰዱሽ፤ ኀይለኛውም የምሥራቅ ነፋስ አንገላትቶ በባሕሩ ውስጥ ሰባበረሽ።


ታላቅ ዐውሎ ነፋስ በባሕሩ ላይ ስለ ተነሣ ማዕበሉ ጀልባይቱን ሊያሰጥማት ደረሰ፤ ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር።


ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ተነሥቶ ውሃው በጀልባው እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ ጀልባውን ይመታ ጀመር።


መርከቡም ስለ ተገፋና ነፋሱን መቋቋም ስላልቻለ ዝም ብለን በነፋሱ እየተነዳን ሄድን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios