Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 23:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ጳውሎስም “ወንድሞቼ ሆይ! የካህናት አለቃ መሆኑን አላወቅሁም ነበር፤ ምክንያቱም ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር’ የሚል ተጽፎአል” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጳውሎስም፣ “ወንድሞች ሆይ፤ ሊቀ ካህናት መሆኑን ባለማወቄ ነው፤ ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ አትናገር’ ተብሎ ተጽፏልና” አላቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጳውሎስም “ወንድሞች ሆይ! ሊቀ ካህናት መሆኑን ባላውቅ ነው፤ ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር፤’ ተብሎ ተጽፎአልና፤” አላቸው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ጳው​ሎ​ስም፥ “ወን​ድ​ሞች፥ ሊቀ ካህ​ናት መሆ​ኑን አላ​ው​ቅም መጽ​ሐፍ ‘በሕ​ዝ​ብህ አለቃ ላይ ክፉ አት​ና​ገር’ ይላ​ልና” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ጳውሎስም፦ ወንድሞች ሆይ፥ ሊቀ ካህናት መሆኑን ባላውቅ ነው፤ በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር ተብሎ ተጽፎአልና አላቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 23:5
6 Referências Cruzadas  

“በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል አትናገር፤ የሕዝብህንም መሪ አትስደብ።


የሚሰማብኝ የለም ብለህ በስውር እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትማ፤ በተኛህበት አልጋህ ላይ ሆነህም ባለጸጋን አትስደብ፤ ምሥጢርህን የሰሙ ነገር ጠላፊዎች ክንፍ እንዳለው ወፍ በረው ሊነግሩብህ ይችላሉ።


እዚያ የነበሩ ሰዎች ጳውሎስን “የእግዚአብሔርን የካህናት አለቃ ትሳደባለህን?” አሉት።


“ከኢየሩሳሌም ከወጣሁ ብዙ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ለወገኖቼ የሚሆን የእርዳታ ገንዘብና ለእግዚአብሔር የሚሰጥ መባ ይዤ መጣሁ።


በተለይም እነዚያን ርኩስ የሆነውን የሥጋ ፍትወታቸውን የሚከተሉትንና የእግዚአብሔርን ሥልጣን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ደፋሮችና ትዕቢተኞች ስለ ሆኑ የሰማይ ሥልጣናትን ሲሳደቡ አይፈሩም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios