Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 1:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “ይህም የሆነበት ምክንያት በመዝሙር መጽሐፍ፥ ‘መኖሪያው ባዶ ይሁን፤ ማንም አይኑርበት፤ ደግሞም ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰድበት’ የሚል ተጽፎ ስለ ነበር ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ጴጥሮስም በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “በመዝሙር መጽሐፍ፣ ‘መኖሪያው ባድማ ትሁን፤ የሚኖርባትም አይገኝ’ ደግሞም፣ ‘ሹመቱንም ሌላ ይውሰደው’ ተብሎ ተጽፏል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በመዝሙር መጽሐፍ ‘መኖሪያው ምድረ በዳ ትሁን፤ የሚኖርባትም አይኑር፤’ ደግሞም ‘ሹመቱን ሌላ ይውሰዳት፤’ ተብሎ ተጽፎአልና።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በመ​ዝ​ሙር መጽ​ሐፍ ‘መኖ​ሪ​ያዉ ምድረ በዳ ትሁን፤ በው​ስ​ጧም የሚ​ኖር አይ​ኑር፤ ሹመ​ቱ​ንም ሌላ ይው​ሰድ’ ተብሎ ተጽ​ፎ​አ​ልና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በመዝሙር መጽሐፍ፦ “መኖሪያው ምድረ በዳ ትሁን የሚኖርባትም አይኑር፤” ደግሞም፦ “ሹመቱን ሌላ ይውሰዳት” ተብሎ ተጽፎአልና።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 1:20
9 Referências Cruzadas  

መኖሪያቸው ወና ይሁን፤ በቤታቸው ውስጥ አንድም ሰው አይኑር።


ከዚህም በኋላ በእነዚያ በቀድሞዎቹ ድንጋዮች ምትክ ሌሎች አዳዲስ ድንጋዮች ተገንብተው ቤቱ በአዲስ ጭቃ ይመረግ።


ዳዊት እኮ ራሱ በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ፦ ‘ጌታ ለጌታዬ ጠላቶችህን በእግርህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው’ ይላል።


ኢየሱስም፥ “ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ለሙሴ በተሰጠው ሕግ፥ በነቢያትና በመዝሙር መጻሕፍት ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም አለበት ብዬ የነገርኳችሁ ቃል ይህ ነው” አላቸው።


“ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት ሰዎች መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ፥ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል መፈጸም ነበረበት።


የምንጸልየውም ይሁዳ ወደ ራሱ ስፍራ ሲሄድ የተወውን አገልግሎትና ሐዋርያነት በመቀበል የሚተካውን እንድትገልጥልን ነው።”


እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት በማስነሣቱ ይህንኑ ተስፋ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞታል፤ ይህም በሁለተኛው መዝሙር፥ ‘አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤’ ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios