Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ሳሙኤል 18:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ከዚህም በኋላ ኢዮአብ አገልጋዩ የነበረውን አንድ ኢትዮጵያዊ ጠርቶ “ያየኸውን ሁሉ ሄደህ ለንጉሡ ንገር” አለው፤ አገልጋዩም እጅ ነሥቶ ሮጠ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከዚያም ኢዮአብ ለኢትዮጵያዊው፣ “ሂድና ያየኸውን ለንጉሡ ንገር” አለው፤ ኢትዮጵያዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከዚያም ኢዮአብ ለኢትዮጵያዊው፥ “ሂድና ያየኸውን ለንጉሡ ንገር” አለው። ኢትዮጵያዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ኢዮ​አ​ብም ኩሲን፥ “ሂድ፤ ያየ​ኸ​ው​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ንገር” አለው። ኩሲም ለኢ​ዮ​አብ ሰግዶ ወጣ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ኢዮአብም ኵሲን፦ ሂድ ያየኸውንም ለንጉሡ ንገር አለው። ኵሲም ለኢዮአብ እጅ ነሥቶ ሮጠ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ሳሙኤል 18:21
4 Referências Cruzadas  

ኢዮአብም “አይሆንም፤ ዛሬ አንተ ይዘኸው የምትሄድ ምንም ዐይነት መልካም ወሬ የለም፤ ምናልባት ሌላ ቀን ይህን ልታደርግ ትችላለህ፤ ዛሬ ግን የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ ይህን ባታደርግ ይሻላል” አለው።


አሒማዓጽም “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ ስለዚህ እኔም ወሬውን እንዳደርስ ፍቀድልኝ” አለ። ኢዮአብ ግን “ልጄ ሆይ፥ ስለምን ይህን ማድረግ ፈለግኽ? ይህን ስላደረግህ ምንም ሽልማት አታገኝም እኮ” አለው።


አሒማዓጽም እንደገና “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ እኔ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ኢዮአብም “እንግዲያውስ ሂድ” አለው፤ ስለዚህም አሒማዓጽ በዮርዳኖስ ሸለቆ በሚያመራው መንገድ ሲሮጥ ሄዶ ወዲያውኑ ኢትዮጵያዊውን ቀደመው።


ቀጥሎም ኢትዮጵያዊው አገልጋይ እዚያ ደረሰና ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! የምሥራች ቃል ይዤልህ መጥቼአለሁ፤ በአንተ ላይ በዐመፅ የተነሣሡብህን ድል እንድታደርግ ዛሬ እግዚአብሔር ረድቶሃል!” አለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios