Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ቆሮንቶስ 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የኋለኛው ክብር እጅግ የላቀ ከመሆኑ የተነሣ ያለፈው ክብር ምንም እንዳልነበረው ይቈጠራል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከዚህ በፊት ክቡር የነበረው የላቀ ክብር ካለው ጋራ ሲወዳደር ክብር የሌለው ሆኗል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በእርግጥ ያ ከብሮ የነበረው እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት ክብሩን አጥቶአል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በዚህ ፍጹም ክብር ባነ​ጻ​ጸ​ሯት ጊዜ የከ​በ​ረ​ችው እን​ዳ​ል​ከ​በ​ረች ትሆ​ና​ለ​ችና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚህ ነገር ክብሩን አጥቶአልና።

Ver Capítulo Cópia de




2 ቆሮንቶስ 3:10
11 Referências Cruzadas  

እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጨረቃ እንኳ ደማቅ አይደለችም፤ ከዋክብትም በእርሱ ፊት ንጹሖች አይደሉም።


የሠራዊት እምላክ ስለሚነግሥ ጨረቃ ትጨልማለች፥ ፀሐይም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ እርሱ በኢየሩሳሌም፥ በጽዮን ተራራ ላይ ሆኖ ያስተዳድራል፤ የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ ክብሩን ያያሉ።


“የዚህ ቤተ መቅደስ የቀድሞ ክብሩ እንዴት እንደ ነበረ ያየ ሰው በእናንተ መካከል አለን? ዛሬስ እንዴት ሆኖ ታዩታላችሁ? ይህ በእናንተ ዘንድ እንደሌለ የሚቈጠር አይደለምን?


ንጉሥ ሆይ! በመንገድ ሳለሁ ልክ እኩለ ቀን ሲሆን ከፀሐይ ብርሃን የሚበልጥ ብርሃን አየሁ፤ ይህም ብርሃን በእኔና ከእኔ ጋር በሚጓዙት ሰዎች ዙሪያ ከሰማይ አበራ።


ያ እየደበዘዘ ይሄድ የነበረው ነገር ይህን ያኽል ክብር ከነበረው፥ ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖረው ነገርማ እንዴት እጅግ የበለጠ ክብር አይኖረውም!


ሰዎች የተኰነኑበት አገልግሎት ይህን ያኽል ክብር ካለው ሰዎች የሚጸድቁበት አገልግሎትማ እንዴት እጅግ የበለጠ ክብር አይኖረውም?


“በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው!” የሚል ድምፅ ከታላቁ ክብር በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ገናናነትን ተቀብሎአል።


ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios