Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 13:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህ በኋላ አቢያ ኰረብታማ በሆነ በኤፍሬም አገር ወደሚገኘው ወደ ጸማራይም ተራራ ወጥቶ ቆመ፤ ድምፁን ከፍ በማድረግም ለኢዮርብዓምና ለእስራኤላውያን በሙሉ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ አድምጡኝ!

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አብያ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ፣ እንዲህ አለ፤ “ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ስሙኝ!

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አብያም በተራራማው በኤፍሬም አገር ባለው በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፦ “ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አብ​ያም በኤ​ፍ​ሬም ተራራ ባለው በሳ​ም​ሮን ተራራ ላይ ቆሞ እን​ዲህ አለ፥ “ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አብያም በተራራማው በኤፍሬም አገር ባለው በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ“ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 13:4
5 Referências Cruzadas  

አርዋዳውያን፥ ጸማራውያን፥ ሐማታውያን ነበሩ፤ ዘግይቶም የተለያዩት የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤


በዚህ ጊዜ አቢያ አራት መቶ ሺህ ሠራዊት ይዞ ሲዘምት፥ ኢዮርብዓም ደግሞ ስምንት መቶ ሺህ ወታደሮችን አሰለፈ።


ዐዛርያስም ከንጉሥ አሳ ጋር ለመገናኘት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አሳ ሆይ! አድምጠኝ! እናንተም የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ ሆናችሁ ድረስ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ከፈለጋችሁትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፤


የዮርዳኖስ ሸለቆ ጸማራይም፥ ቤትኤል፥


ኢዮአታም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ወደ ገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ እንዲህ በማለት ወደ እነርሱ ጮኸ፤ “እናንተ የሴኬም ሰዎች! እኔን ብታዳምጡኝ እግዚአብሔርም እናንተን ያዳምጣችኋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios