Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ጢሞቴዎስ 5:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 አንዲት አማኝ የሆነች ሴት በቤትዋ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ቢኖሩአት የቤተ ክርስቲያን ሸክም እንዳይሆኑ እርስዋ ትርዳቸው፤ በዚህ ዐይነት ቤተ ክርስቲያን ፈጽሞ ረዳት የሌላቸውን ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች መርዳት ትችላለች።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አማኝ የሆነች ማንኛዋም ሴት በቤተ ሰቧ ውስጥ መበለቶች ቢኖሯት፣ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ መበለቶችን ብቻ መርዳት እንድትችል እርሷው ትርዳቸው እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ሸክም እንዲሆኑ አትተዋቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አማኝ የሆነች ማንም ሴት መበለታት ዘመዶች ቢኖሩአት፥ እነርሱን ትርዳቸው፤ ቤተክርስትያንም በእርግጥ እርዳታ የሚያሻቸውን መበለታትን መርዳት እንድትችል ሸክም አይሁኑባት።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ባልቴቶች ያሉት የሚያምን ቢሆን ወይም የምታምን ብትሆን፥ ይርዱአቸው፤ ቤተ ክርስቲያንም እውነተኞችን ባልቴቶች እንድትረዳ አይክበዱባት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ባልቴቶች ያሉት የሚያምን ቢሆን ወይም የምታምን ብትሆን፥ ይርዱአቸው፥ ቤተ ክርስቲያንም እውነተኞችን ባልቴቶች እንድትረዳ አይክበዱባት።

Ver Capítulo Cópia de




1 ጢሞቴዎስ 5:16
4 Referências Cruzadas  

እንዲሁም ልጆችን በሚገባ በማሳደግ፥ እንግዳን በመቀበል፥ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፥ የተቸገሩትን በመርዳትና ማንኛውንም በጎ ሥራ ሁሉ በማከናወን ለመልካም ሥራም ሁሉ የተጋች መሆን አለባት።


ለራሱ ዘመዶች፥ ይልቁንም ለቅርብ ቤተሰቦቹ የማያስብ ሃይማኖቱን የካደ ነው፤ እንዲያውም ከማያምን ሰው እንኳ የባሰ ክፉ ነው።


ከስድሳ ዓመት በታች የሆነችን ባልዋ የሞተባትን ሴት በመበለቶች መዝገብ አትጻፍ፤ ደግሞም አንድ ባል ብቻ ያገባች እንድትሆን ያስፈልጋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios