Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እነሆ እኔ የአንተ እንዲሆን በመረጥከውና ከብዛቱ የተነሣ ሊቈጠር በማይችል ሕዝብ መካከል እገኛለሁ፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ባሪያህ አንተ በመረጥኸው ሕዝብ፣ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር በማይችል ታላቅ ሕዝብ መካከል ይገኛል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እነሆ እኔ የአንተ እንዲሆን በመረጥከውና ከብዛቱ የተነሣ ሊቆጠር በማይችል ሕዝብ መካከል እገኛለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ባሪ​ያ​ህም ያለው አንተ በመ​ረ​ጥ​ኸው ሕዝ​ብህ፥ ስለ ብዛ​ቱም ይቈ​ጠር ዘንድ በማ​ይ​ቻል በታ​ላቅ ሕዝብ መካ​ከል ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ባሪያህም ያለው አንተ በመረጥኸው ሕዝብህ ስለ ብዛቱም ይቈጠርና ይመጠን ዘንድ በማይቻል በታላቅ ሕዝብ መካከል ነው።

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 3:8
12 Referências Cruzadas  

ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ የምድር አሸዋ ሊቈጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር እንዲሁ ሊቈጠር የማይቻል ይሆናል።


ቀጥሎም እግዚአብሔር አብራምን ወደ ውጪ አወጣውና “ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ከዋክብትን መቊጠር ትችል እንደሆን ሞክር፤ እንግዲህ የአንተም ዘሮች እንደዚህ ይበዛሉ” አለው።


እኔም ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም ጠላቶቻቸውን ድል ነሥተው ከተሞቻቸውን ይይዛሉ።


የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ እየበሉና እየጠጡ ዘወትር ደስ ይሰኙ ነበር፤


ዳዊት ለኢዮአብና ለሌሎቹ የጦር መኰንኖች “በመላው እስራኤል ከአገሪቱ ዳር እስከ ዳር፥ ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሄዳችሁ ሕዝቡን ቊጠሩ፤ እኔ በእስራኤል ምን ያኽል ሕዝብ እንዳለ ማወቅ እፈልጋለሁ” የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው።


ከበጎች እረኝነት አውጥቶም፥ የእስራኤል ንጉሥና የእግዚአብሔር ሕዝብ ጠባቂ አደረገው።


ፊቴን በምሕረት ወደ እናንተ እመልሳለሁ፤ ዘራችሁን አበዛለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።


እግዚአብሔር የእርሱ ሕዝብ ያደርጋችሁ ዘንድ ወዶአልና ስለ ታላቅ ስሙ እናንተን ሕዝቡን አይተውም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios