Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ቆሮንቶስ 9:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔር ይህን ያለው ስለ እኛ በማሰብ አይደለምን? የሚያርስ ገበሬ በተስፋ እንዲያርስ፥ የሚያበራይም በተስፋ እንዲያበራይ፥ በዚህ ዐይነት ሁሉም ድርሻውን እንዲያገኝ ይህ የተጻፈው በእርግጥ ስለ እኛ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ይህን የተናገረው በርግጥ ስለ እኛ አይደለምን? የተጻፈው በትክክል ስለ እኛ ነው፤ ዐራሹ የሚያርሰው፣ አበራዩ የሚያበራየው ከምርቱ ድርሻ እንዳለው ተስፋ በማድረግ ነውና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ይህን የሚለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይደለምን? በእርግጥ ስለ እኛ ተጽፎአል፥ ይኸውም የሚያርስ በተስፋ እንዲያርስ፥ የሚያበራይም እንዲካፈል በተስፋ ሊያበራይ ስለሚገባው ነው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ይህን የሚ​ለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይ​ደ​ለ​ምን? የሚ​ያ​ርስ በተ​ስፋ ሊያ​ርስ፥ የሚ​ያ​በ​ራ​ይም እን​ዲ​ካ​ፈል በተ​ስፋ ሊያ​በ​ራይ ስለ​ሚ​ገ​ባው በእ​ው​ነት ስለ እኛ ተጽ​ፎ​አል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ይህን የሚለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይደለምን? የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ የሚያበራይም እንዲካፈል በተስፋ ሊያበራይ ስለሚገባው በእውነት ስለ እኛ ተጽፎአል።

Ver Capítulo Cópia de




1 ቆሮንቶስ 9:10
9 Referências Cruzadas  

እርሱ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለምትሰጡት አገልግሎት የድካም ዋጋችሁ ስለ ሆነ የተረፈውንም እናንተና ቤተሰቦቻችሁ በየትኛውም ስፍራ ሆናችሁ መመገብ ትችላላችሁ፤


እነዚያ ቀኖች ባያጥሩማ ኖሮ አንድም ሰው መዳን ባልቻለ ነበር፤ ነገር ግን ስለ ተመረጡት ሰዎች እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ።


ከቅዱሳት መጻሕፍት በምናገኛቸው ትዕግሥትና መጽናናት ተስፋ ይኖረን ዘንድ ቀደም ብለው የተጻፉት ሁሉ ትምህርት እንዲሆኑን ተጽፈዋል።


እኛ ለእግዚአብሔር አብረን የምንሠራ አገልጋዮች ነን፤ እናንተም የእግዚአብሔር እርሻና የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ።


ይህ ሁሉ ለእናንተ ጥቅም የሆነው ጸጋ ተትረፍርፎ ለብዙ ሰዎች በደረሰ መጠን ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆነው ምስጋና እንዲበዛ ነው።


በሥራ የሚደክም ገበሬ ከሥራው ከሚገኘው ፍሬ የመጀመሪያውን ማግኘት ይገባዋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios