Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ቆሮንቶስ 7:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔር በጠራህ ጊዜ ባሪያ ነበርክን? ብትሆንም ግድ የለም፤ አትጨነቅበት፤ ነጻ የመውጣት ዕድል ብታገኝ ግን ይህ ዕድል አያምልጥህ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በተጠራህ ጊዜ ባሪያ ነበርህን? በዚህ አትጨነቅ፤ ነጻነትህን ማግኘት ከቻልህ ግን ነጻነትህን ተቀበል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ባርያ ሆነህ ተጠርተህ እንደሆነ አይገድህም፤ ነጻ ልትወጣ ቢቻልህ ግን ነጻነትን ተቀበል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አንተ ባርያ ሳለህ ብታ​ምን አያ​ሳ​ዝ​ንህ፤ የሚ​ቻ​ልህ ከሆነ ግን ነጻ​ነ​ት​ህን አግኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ባሪያ ሆነህ ተጠርተህ እንደ ሆነ አይገድህም፤ አርነት ልትወጣ ቢቻልህ ግን አርነትን ተቀበል።

Ver Capítulo Cópia de




1 ቆሮንቶስ 7:21
14 Referências Cruzadas  

“ስለዚህ ‘ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን?’ እያላችሁ በማሰብ አትጨነቁ።


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።


አይሁድም ብንሆን የግሪክ ሰዎች ብንሆን፤ ባሪያዎችም ብንሆን፥ ነጻ ሰዎችም ብንሆን፥ አንድ ሰውነት ለመሆን በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀናል፤ ሁላችንም ከዚሁ ከአንዱ መንፈስ ጠጥተናል።


ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር በጠራው ጊዜ በነበረበት ሁኔታ ይኑር።


ባሪያ ሆኖ ሳለ በጌታ የተጠራ ሰው በጌታ ነጻነትን አግኝቶአል፤ እንዲሁም ነጻ ሆኖ ሳለ የተጠራ ሰው የክርስቶስ ባሪያ ነው።


ሁላችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ስለ ሆናችሁ በአይሁዳዊና በግሪካዊ፥ በአገልጋይና በጌታ፥ በወንድና በሴት መካከል ምንም ልዩነት የለም።


ደግሞም ይህን የምለው ለኑሮዬ የሚያስፈልገኝን በማጣቴ አይደለም፤ እኔማ “ያለኝ ነገር ይበቃኛል” ማለትን ተምሬአለሁ።


ስለዚህ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፥ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ።


በዚህ ሁኔታ በግሪካዊና በአይሁዳዊ፥ በተገረዘና ባልተገረዘ፥ በሠለጠነ አረመኔና ባልሠለጠነ አረመኔ፥ ነጻነት በሌለውና ነጻነት ባለው ሰው መካከል ልዩነት የለም፤ ክርስቶስ ሁሉም ነው፤ በሁሉም ነው።


ከገንዘብ ፍቅር ራቁ፤ ያላችሁ ይብቃችሁ፤ እግዚአብሔር “ከቶ አልጥልህም፤ ፈጽሞም አልተውህም” ብሎአል።


እርሱ ለእናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሐሳብ ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios