Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘካርያስ 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እኔም፦ “ምንድን ናት?” አልኩት። እርሱም፦ “ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት” አለኝ። ደግሞም፦ “ይህ ነው በምድር ሁሉ ያለ የእነርሱ በደል” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እኔም፣ “ምንድን ነው?” አልሁት። እርሱም፣ “የኢፍ መስፈሪያ ነው” አለኝ። ቀጥሎም “ይህ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ያለው የሕዝቡ በደል ነው” አለኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እኔም “ይህ ነገር ምንድን ነው?” አልኩት። እርሱም “በምድሪቱ ሁሉ ላይ የሚሠራውን ኃጢአት የሚያመለክት ቅርጫት ነው” አለኝ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እኔም፦ ምንድር ናት? አልሁ። እርሱም፦ ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት አለኝ። ደግሞም፦ በምድር ሁሉ ላይ ያለ በደላቸው ይህ ነው አለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እኔም፦ ምንድር ናት? አልሁ። እርሱም፦ ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት አለኝ። ደግሞም፦ በምድር ሁሉ ላይ ያለ በደላቸው ይህ ነው አለ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘካርያስ 5:6
8 Referências Cruzadas  

ትክክለኛም ሚዛን፥ ትክክለኛም መመዘኛ፥ ትክክለኛም የኢፍ መስፈሪያ፥ ትክክለኛም የኢን መስፈሪያ ይኑሩአችሁ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።


ችግረኛውን የምትረግጡ፥ የአገሩንም ድሀ የምታጠፉ ይህን ስሙ፤


እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህልን እንድንሸጥ መባቻው መቼ ያልፋል? ስንዴውንም ለሽያጭ ገበያ ለማቅረብ ሰንበት መቼ ያበቃል? የኢፍ መስፈሪያውንም እናሳንሳለን፥ ሰቅሉንም እናበዛለን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እናታልላለን፥


ድሀውን በብር ችግረኛውንም በአንድ ጥንድ ጫማ እንገዛለን፥ የስንዴውን ገለባ እንሸጣለን።”


በክፉ ቤት የክፋት መዝገብ፥ አስጸያፊ ሐሰተኛ መስፈሪያ አሁንም አለን?


በዚያን ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን፥ የጌታቸውን ቤት በዓመፅና በማታለል የሚሞሉትን እቀጣለሁ።


ከዚያም የእርሳሱን መክሊት አነሡት፥ እነሆም፥ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios