Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማሕልየ መሓልይ 8:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ ፍቅርን እንዳታስነሡት እንዳታነሣሡትም አስምላችኋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት አማፅናችኋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅ ሆይ! ፍቅር ራሱ ወዶ እስኪነሣ ድረስ ቀስቅሳችሁ እንዳታስነሡት ዐደራ እላችኋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ ፍቅርን እንዳታስነሡት እንዳታነሣሡትም አምላችኋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ማሕልየ መሓልይ 8:4
3 Referências Cruzadas  

እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፥ ውብም ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ፥ ፍቅርን እንዳታስነሱትና እንዳታነሣሡት በሚዳቋ በምድረ በዳም ዋላ አስምላችኋለሁ።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈንጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ፥ ፍቅርን እንዳታስነሡትና እንዳታነሣሡት በሚዳቋ በምድረ በዳም ዋላ አስምላችኋለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios