Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 79:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የባርያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፥

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የባሪያዎችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣ የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፣ ምግብ አድርገው ሰጡ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የሕዝብህን ሬሳ ለሰማይ ወፎችና የታማኞችህን ሥጋ ለአራዊት ምግብ አድርገው ሰጡ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በኤ​ፍ​ሬ​ምና በብ​ን​ያም በም​ና​ሴም ፊት ኀይ​ል​ህን አንሣ፥ እኛ​ንም ለማ​ዳን ና።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 79:2
7 Referências Cruzadas  

ሰይፍን ለመግደል፥ ውሾችንም ለመጐተት፥ የሰማያትንም ወፎች የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ ዐራቱን ዓይነት ጥፋት ልኬባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።


በክፉ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም አይቀበሩምም፥ በመሬትም ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፥ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።


በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፥ በጠላቶቻቸውም ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፥ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ።


ለጠላቶቻቸው እጅ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።


የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድርም አራዊት መብል ይሆናል፥ የሚያስፈራራቸውም የለም።


በሰዎች ላይ ጭንቀትን አመጣለሁ፤ እንደ ዕውርም ይሄዳሉ፥ በጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርተዋልና፤ ደማቸው እንደ ትቢያ ይፈስሳል፥ ሥጋቸውም እንደ ጉድፍ ይጣላል።


ሬሳህ የሰማይ አሞሮችና የምድር አራዊት መብል ይሆናል፤ የሚያባርራቸውም አይኖርም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios