Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 78:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ነገር ግን ይበድሉት ዘንድ እንደገና ደገሙ፥ ልዑልንም በምድረ በዳ አስቈጡት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እነርሱ ግን በምድረ በዳ በልዑል ላይ በማመፅ፣ በርሱ ላይ ኀጢአት መሥራታቸውን ቀጠሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እነርሱ ግን እግዚአብሔርን በመበደል ኃጢአት መሥራት ቀጠሉ፤ በበረሓም በልዑል እግዚአብሔር ላይ ዐመፁ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 78:17
9 Referências Cruzadas  

ከዚህም ሁሉ ጋር እንደገና በደሉ፥ ተኣምራቱንም አላመኑም፥


እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፤ ስለዚህ ጠላታቸው ሆነ፤ እርሱ ራሱ ተዋጋቸው።


እነርሱ ግን ዐመፁብኝ ይሰሙኝም ዘንድ አልወደዱም፥ ሁሉም እያንዳንዱ የዓይኑን ርኩሰት አልጣለም የግብጽንም ጣዖታት አልተወም፤ በዚህም ጊዜ፦ በግብጽ ምድር መካከል ቁጣዬን እፈጽምባቸው ዘንድ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።


እኔ ዓመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፥ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በጌታ ላይ ዐምፃችኋል፥ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል?


በኮሬብም የጌታን ቁጣ ቀሰቀሳችሁ፥ ጌታም ሊያጠፋችሁ እስኪነሳ አስቆጣችሁት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios