Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 62:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የዳዊት መዝሙር

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ድነቴም የሚመጣልኝ ከርሱ ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የሚያድነኝ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አም​ላኬ፥ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ እገ​ሠ​ግ​ሣ​ለሁ፤ ነፍሴ አን​ተን ተጠ​ማች፥ እን​ጨ​ትና ውኃ በሌ​ለ​በት ምድረ በዳ ሥጋ​ዬን ለአ​ንተ እን​ዴት ልዘ​ር​ጋ​ልህ

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 62:1
26 Referências Cruzadas  

ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ ይሠሩ የነበሩት ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።


ከኤዶታም የኤዶታም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ጽሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መቲትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ክብር በመሰንቆ ትንቢት ከተናገረው ከአባታቸው ከኤዶታም ትእዛዝ በታች ነበሩ።


ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከጌታ ዘንድ ነው።


እነሆ፥ የአገልጋዮች ዐይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የአገልጋዪቱም ዐይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ ዓይናችን ወደ ጌታ አምላካችን ነው።


አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም፥ ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።


በጌታ ተስፋ አድርግ፥ በርታ፥ ልብህም ይጽና፥ በጌታ ተስፋ አድርግ።


ነፍሳችን ጌታን ተስፋ ታደርገዋለች፥ ረዳታችንና ጋሻችን እርሱ ነውና።


የጻድቃን መድኃኒታቸው በጌታ ዘንድ ነው፥ በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው።


በጌታ ጽና በተዕግሥትም ጠብቀው። መንገዱም በቀናችለትና በሚያደባ ሰው አትቅና።


ለመዘምራን አለቃ፥ ለኤዶታም፥ የዳዊት መዝሙር።


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።


ነፍሴ በጸጥታ እግዚአብሔርን ትጠብቅ የለምን? መድኃኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት የምስጋና መዝሙር።


ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የአሳፍ መዝሙር።


እነሆ፤ ጌታ መዳኛዬ ነው፤ እታመናለሁ፤ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ የመዳኔ ምክንያትም ሆኖአል።”


ጌታም የፍርድ አምላክ ነው፤ ስለ ሆነም ጌታ ይራራላችኋልና ይታገሣል፤ ሊምራችሁም ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።


ጌታን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።


በእውነት ኮረብቶች ሐሰት ናቸው፥ በተራሮችም ላይ ሁከት ነው፤ በእውነት የእስራኤል መዳን በአምላካችን በጌታ ነው።”


ጤት። ጌታ በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።


ከልዑል አፍ ክፉና መልካም ነገር አይወጣምን?


እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ ገበሬ መሬቱ መልካምን ፍሬ እስከሚሰጥ ድረስ እንዴት እንደሚታገሥ፥ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እንዴት እንደሚጠባበቅ አስተውሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios