Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 59:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፥ አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከአፋቸው ስለሚወጣው ኀጢአት፣ ከከንፈራቸውም ስለሚሰነዘረው ቃል፣ በትዕቢታቸው ይያዙ። ስለ ተናገሩት መርገምና ውሸት፣

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከአንደበታቸው ኃጢአት አይጠፋም፤ ንግግራቸው ሁሉ ኃጢአት የሞላበት ነው፤ እነርሱ ስለሚራገሙና ስለሚዋሹ በትዕቢታቸው ይያዙ!

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ እር​ሱም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ንን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 59:12
20 Referências Cruzadas  

ከምድር አሕዛብ አለቆች ዘንድ ማስተዋልን ያስወግዳል፥ መንገድም በሌለበት በረሃ ያቅበዘብዛቸዋል።


በክፉዎች ትዕቢት ምስኪኖች ይሰደዳሉ፥ ባሰቡት ተንኰላቸው ተጠመዱ።


አፉ በመርገም፥ በሽንገላና በዐመፃ የተመላ ነው፥ ከምላሱ በታች ተንኰልና ክፋት አሉ።


አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።


ቅኖችን ጽድቃቸው ይታደጋቸዋል፥ ወስላቶች ግን በምኞታቸው ይጠመዳሉ።


ክፉ ሰው በከንፈሩ ኃጢአት ይጠመዳል፥ ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል።


የሰነፍ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሩም ለነፍሱ ወጥመድ ነው።


በአፍህ ቃል ከተጠመድህ፥ በአፍህ ቃል ከተያዝህ።


የተነሡብኝን ሰዎች ከንፈሮች ቀኑንም ሁሉ ያሰቡብኝን አሳባቸውን ሰማህ።


በሚሄዱባቸው አሕዛብ መካከል ርኩሰታቸውን ሁሉ እንዲናገሩ ከእነርሱ ጥቂቶች ከሰይፍ፥ ከራብና ከቸነፈር አስቀራለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


መራገምና መዋሸት፥ መግደልና መስረቅ፥ ማመንዘርም ገደባቸውን አልፈዋል፤ ደም ማፍሰስ ደም ማፍሰስን አስከትሏል።


በዚያ ቀን በእኔ ላይ አምፀሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም፤ በኩራትሽ የተደሰቱትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ላይ ዳግመኛ አትታበዪም።


ሕዝቡም ሁሉ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” ብለው መለሱ።


እንዲህም አሉት፦ “ጌታ ሆይ! ያ አሳች በሕይወት ሳለ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ’ እንዳለ ትዝ አለን።


እነርሱ ግን “ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ በይሁዳ ሁሉ እያስተማረ ሕዝቡን ያውካል” በማለት አጥብቀው ተናገሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios