Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 38:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ከቁስሌ ገለል ብለው ቆሙ፥ ዘመዶቼም ርቀው ቆሙ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ሊያጠፉኝ ዛቱ፤ ቀኑንም ሙሉ ተንኰል ይሸርባሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ወጥመድ ይዘረጉብኛል፤ ሊጐዱኝ የሚያቅዱ ሊያጠፉኝ ይዝታሉ፤ በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥ ልቅ​ሶ​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥ ቸልም አት​በ​ለኝ፤ እኔ በም​ድር ላይ መጻ​ተኛ ነኝና፥ እንደ አባ​ቶ​ችም ሁሉ እን​ግዳ ነኝና።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 38:12
18 Referências Cruzadas  

“ወንድሞቼን ከእኔ ዘንድ አራቀ፥ የሚያውቁኝም አጥብቀው ተለዩኝ።


እንደ አንበሳ በዱር በስውር ይሸምቃል፥ ድሀውን ለመንጠቅ ያደባል፥ ድሀውን ይነጥቀዋል በአሽክላውም ይስበዋል።


ኃጢአተኞች ወጥመድን ዘረጉብኝ፥ ከትእዛዝህ ግን አልሳትሁም።


አቤቱ፥ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፥ እርምጃዬንም ሊያሰናክሉ ከመከሩ ከዓመፀኞች አድነኝ።


ከሰወሩብኝ ወጥመድ፥ ዓመፅንም ከሚያደርጉ ሰዎች ዕንቅፋት ጠብቀኝ።


በጠላቶቼ ዘንድ ተነወርኹ፥ ይልቁንም በጎረቤቶቼ ዘንድ፥ ለሚያውቁኝም ፍርሃት ሆንሁ፥ በሜዳ ያዩኝም ከእኔ ሸሹ።


በእርጋታ በምድሪቱ ለተቀመጡት ሰላምን አይናገሩምና፥ በቁጣም ሽንገላን ይመክራሉ።


ነፍሴን ሊያጠፉ የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐስቁሉም፥ ክፉትን በእኔ ላይ የሚያስቡ ይዋረዱ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።


እኔስ፦ “አቤቱ፥ ማረኝ፥ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ።


አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥ በኃይልህም ፍረድልኝ።


ለወንድሞቼ እንደ ሌላ፥ ለእናቴ ልጆችም እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው።


የሚያውቁኝን ከእኔ አራቅህ፥ በእነርሱ ዘንድ አጸያፊ አደረግኸኝ፥ ተዘግቶብኛል፥ መውጫም የለኝም።


ድሀን ሰው ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፥ ይልቁንም ወዳጆቹ ከእርሱ ይርቃሉ። እነርሱንም በቃል ቢከተላቸው አንዳች አይረቡትም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios