Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 140:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለክፉዎች አትስጠኝ፥ ተንኮላቸው እንዲሳካ አትፍቀድ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ዙሪያዬን የከበቡኝ ሰዎች ራስ፣ የከንፈራቸው መዘዝ ይጠምጠምበት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የከበቡኝ ጠላቶቼ በእኔ ላይ ያቀዱትን ሤራ በእነርሱ ላይ እንዲፈጸም አድርግ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከሰ​ወ​ሩ​ብኝ ወጥ​መድ፥ ዐመ​ፃ​ንም ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች እን​ቅ​ፋት ጠብ​ቀኝ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 140:9
11 Referências Cruzadas  

እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል። ድንገተኛ ፍላጻም ያቈስላቸዋል፥


ጉድጓድን ማሰ ቈፈረም። በሠራውም ጉድጓድ ይወድቃል።


እንደ በደላቸውም፥ እንደ ክፋታቸውም ፍዳቸውን ይከፍላቸዋል፥ ጌታ አምላካችን ያጠፋቸዋል።


የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ማፍለቂያ ናት፥ የክፉዎች አፍ ግን ዐመፅን ይሸፍናል።


በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፥ የክፉዎች አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል።


ክፉ ሰው በከንፈሩ ኃጢአት ይጠመዳል፥ ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል።


የሰነፍ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሩም ለነፍሱ ወጥመድ ነው።


ሕዝቡም ሁሉ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” ብለው መለሱ።


ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ ‘እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ ጌታ ይህን ሁሉ አላደረገም’ እንዳይሉ፥ ስለ ጠላት ትንኮሳ አሰብኩ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios