Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 134:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በሌሊት በቤተ መቅደስ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፥ ጌታንም ባርኩ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በመቅደሱ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፤ እግዚአብሔርንም ባርኩ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በመቅደሱ እጆቻችሁን ለጸሎት ዘርግታችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ!

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት አደ​ባ​ባይ የም​ት​ቆሙ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 134:2
10 Referências Cruzadas  

ዕዝራም ታላቁን አምላክ ጌታን ባረከ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን በመዘርጋት፦ አሜን፥ አሜን ብለው መለሱ። ራሳቸውን አዘነበሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ለጌታ ሰገዱ።


ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን፥ እጆቼን ማንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ይሁን።


እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፥ አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥


ወደ መቅደስህ ማደሪያ እጄን ባነሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ።


አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፥ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች በደረቅ መሬት፥ ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።


ቸርነትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።


እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።


ቆፍ። ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፥ በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።


ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣ።


እንግዲህ በሁሉ ስፍራ ያሉ ወንዶች ንዴትንና ጥልን አስወግደው የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሡ እንዲጸልዩ ፈቃዴ ነው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios