Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 107:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 በመኰንኖችም ላይ ውርደትን ዘረገፈ፥ መንገድም በሌለበት በምድረ በዳ አንከራተታቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 በመኳንንቱም ላይ መናቅን አዘነበባቸው፤ መውጫ መግቢያው በማይታወቅ በረሓ ውስጥም አንከራተታቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 እግዚአብሔር ልዑላኑን አዋረደ፤ በምድረ በዳም አሸዋ ውስጥ እንዲንከራተቱ አደረገ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 107:40
23 Referências Cruzadas  

እነዚህም የአውራጆች አለቆች ጉልማሶች ከከተማይቱ ወጡ፤ ሠራዊትም ተከተላቸው።


በአለቆች ላይ ንቀትን ያፈስሳል፥ የብርቱዎችንም መታጠቂያ ያላላል።


ከምድር አሕዛብ አለቆች ዘንድ ማስተዋልን ያስወግዳል፥ መንገድም በሌለበት በረሃ ያቅበዘብዛቸዋል።


በበረሃ፥ በምድረ በዳ ተቅበዘበዙ፥ የሚኖሩበትንም ከተማ መንገድ አላገኙም።


ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፥ የዘለዓለምን ውርደት አከናነባቸው።


ሕዝቤን ባትለቅቅ፥ እነሆ በአንተ ላይ፥ በአገልጋዮችህ ላይ፤ በሕዝብህ ላይ፥ በቤቶችህም ላይ የዝንብ መንጋ እልካለሁ፤ የግብፃውያንም ቤቶች፥ የቆሙባትም ምድር ሁሉ በዝንብ መንጋ ይሞላሉ።


ፈርዖንም፦ “ለጌታ አምላካችሁ በምድረ በዳ እንድትሠዉ እለቅቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ርቃችሁ አትሂዱ፥ ጸልዩልኝ” አለ።


አስማተኞችም በአስማታቸው እንዲህ አደረጉ፥ በግብጽም ምድር ላይ እንቁራሪቶችን አወጡ።


ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “እንቁራሪቶቹን ከእኔና ከሕዝቤ እንዲያርቅ ወደ ጌታ ጸልዩልኝ፤ ለጌታም እንዲሠዋ ሕዝቡን እለቅቃለሁ” አላቸው።


ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያንጊዜ የጌታ መልአክ መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።


“በምድረ በዳ በጥማት፥ የነፋስ ጩኸትም በሞላበት በምድረ በዳ አገኘው፥ መከታ ሆነለት፥ ተጠነቀቀለትም፥ እንደ ዐይን ብሌኑም ጠበቀው።


የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባርያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ ትበሉ ዘንድ” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።


የሔቤር ሚስት ያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፥ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፥ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋር ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ።


ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱትም በኋላ የጌታ እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በእባጭ መቅሠፍት መታ።


እነርሱም፥ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዓይነት በመሆኑ፥ በፍልስጥኤማውያን ገዥዎች ቍጥር አምስት የወርቅ ዕባጮችና አምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios