Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 10:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጌታ ለዘለዓለም ንጉሥ ነው፥ አሕዛብ ከምድሩ ይጠፋሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ንጉሥ ነው፤ ሕዝቦችም ከምድሩ ይጠፋሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይኖራል፤ ለሌሎች አማልክት የሚሰግዱ ሕዝቦች ግን ከምድሩ ይጠፋሉ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 10:16
20 Referências Cruzadas  

አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።


መንግሥትህ የዘለዓለም መንግሥት ናት፥ ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው።


ጌታ ለዘለዓለም ይነግሣል፥ ጽዮን ሆይ፥ አምላክሽ ለልጅ ልጅ ነው። ሃሌ ሉያ።


ጌታ የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፥ ጌታ ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።


ከፊታቸውም አሕዛብን አባረረ፥ ርስቱንም በገመድ አካፈላቸው፥ የእስራኤልንም ወገኖች በድንኳናቸው አኖረ።


ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ፥ በጽዮን ልጅ በደጆችዋ በማዳንህ ደስ ይለኛል።


ትክክለኛ ፍርድና ዳኝነት አድርገህልኛልና፥ በጽድቅ እየፈረድህ በዙፋንህ ላይ ተቀመጥህ።


ጌታ ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ ዙፋኑንም ለመፍረድ አዘጋጀ፥


ጌታ ነገሠ፥ ግርማን ተጐናጸፈ፥ ጌታ ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፥ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት።


ጌታ ለዘለዓለም ዓለም ይነግሣል።”


ጌታ ፈራጃችን ነው፥ ጌታ ሕግን ሰጪያችን ነው፥ ጌታ ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።


ጌታ ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቁጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን መቋቋም አይችሉም።


አቤቱ፥ አንተ ለዘለዓለም ትኖራለህ፥ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።


የጌታ የአምላካችሁን ቃል ስላልሰማችሁ፥ ጌታ ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው እንደ አሕዛብ ሁሉ እንዲሁ እናንተም ትጠፋላችሁ።


ለዘመናትም ንጉሥ፥ ለማይሞተው፥ ለማይታየው፥ ብቻውን አምላክ ለሆነው መፈራትና ክብር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios