Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 30:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በአባትዋ የምታላግጥን የእናትዋንም ትእዛዝ የምትንቅን ዐይን የሸለቆ ቁራዎች ይጐጠጉጡአታል፥ አሞራዎችም ይበሉአታል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “በአባት ላይ የምታፌዝ ዐይን፣ የእናትንም ትእዛዝ የምትንቅ፣ የሸለቆ ቍራዎች ይጐጠጕጧታል፤ ጆፌ አሞሮችም ይበሏታል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በአባቱ የሚያፌዝና እናቱ በምታረጅበት ጊዜ የሚንቃት ሰው የሸለቆ ቊራዎች ዐይኖቹን ጐጥጒጠው ያወጡታል፤ ጆፌ አሞራዎችም ይበሉታል።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 30:17
14 Referências Cruzadas  

የአያ ልጅ ሪጽፋ ማቅ ወስዳ፥ በቋጥኝ ላይ ለራሷ አነጠፈች፤ ከመከር ወቅት መጀመሪያ አንሥቶ ዝናብ ከሰማይ በሬሳዎቹ ላይ እስከወረደ ጊዜ ድረስ ቀን የሰማይ ወፎች ሌሊት የዱር አራዊት እንዲነኳቸው አልፈቀደችም፤


ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፥ ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ይንቃል።


አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፥ በጽቅድቅ ጨለማ መብራቱ ይጠፋል።


የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።


አባቱን የሚረግም፥ እናቱንም የማያመሰግን ትውልድ አለ።


ሦስት ነገር ይገርመኛል፥ አራተኛውንም ከቶ አላስተውለውም።


ማናቸውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ፈጽሞ ይገደል፤ አባቱንና እናቱን ሰድቦአልና፥ ደሙ በራሱ ላይ ነው።


“ስሜን የምትንቁ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባርያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔ አባት ከሆንሁ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ?” ይላችኋል የሠራዊት ጌታ። እናንተም፦ “ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?” ብላችኋል።


ሬሳህ የሰማይ አሞሮችና የምድር አራዊት መብል ይሆናል፤ የሚያባርራቸውም አይኖርም።


እርሱም ዳዊትን፥ “እስቲ ወደኔ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞሮችና፥ ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios