Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 24:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 መከራቸው ድንገት ይነሣልና፥ ከሁለቱ የሚመጣውን ጥፋት ማን ያውቃል? (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) የነገሩትን የሚሰማ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ የነገሩትን የሚቀበልን ሰው እግዚአብሔር ይቀበለዋል። ከንጉሥ አንደበት ምንምን ሐሰት ይነገራል አይባልም፥ ከአንደበቱም የሚወጣ ሐሰት የለም። የንጉሥ ቃል ሾተል ናት፥ ለጥፋት የተሰጠችውን ሰው ሰውነት ታጠፋዋለች እንጂ አንድ አካል ብቻ የምታጠፋ አይደለም። ሰይፈ መዓቱ ብትሳል ግን ከወገኑ ጋር ሰውን ታጠፋለች፥ ከአሞሮች ግልገል ወገን የማይበላ እስኪሆን ድረስ እንደ እሳት ነበልባል ታቃጥላለች።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሁለቱም የሚያመጡት መዓት፤ ምን እንደሚሆን ማን ያውቃል?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በእነዚህ ዐመፀኞች ላይ ታላቅ ጥፋት ይደርስባቸዋል፤ የሚደርስባቸው ጥፋት ግን ምን ዐይነት እንደ ሆነ ማን ያውቃል?

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እነርሱ ኀጢአተኞችን ድንገት ይበቀሏቸዋልና፤ የሁለቱንስ ፍርድ ማን ያውቃል?

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 24:22
13 Referências Cruzadas  

አዶንያስም የጠራቸው ሁሉ ፈሩ፥ ተነሥተውም እያንዳንዳቸው በየመንገዳቸው ሄዱ።


የቁጣህን ጽናት ማን ያውቃል? የቁጣህንስ ግርማ ማን ያውቃል?


የንጉሥ ቁጣ እንደ ሞት መልእክተኛ ነው፥ ጠቢብ ሰው ግን ያቈላምጠዋል።


የንጉሥ ቁጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፥ የሚያስቈጣውም ሰው የራሱን ነፍስ ይበድላል።


ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃልና፤ ደግሞም ይነሣል፥ ክፉዎችን ግን መጥፎ ነገር ሲገጥማቸው ይወድቃሉ።


ስለዚህ ጥፋት ድንገት ይደርስበታል፥ ድንገት ይደቅቃል፥ ፈውስም ከቶ የለውም።


ሰውም ጊዜውን አያውቅም፥ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።


ኤፍሬም ትእዛዝን መከተል ፈጽሞ አልወደደምና የተጨቆነና በፍርድ የተጐዳ ሆኖአል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios